ባለፈረጀ ብዙውን የኢትዮጵያ መንግሥት የስለላ ተግባር መከላከል፤ እራስን ከስለላ የመከላከያ ብልሃቶች መመሪያ በአማርኛ ተዘጋጅቷል

eff-logo-name-stack-2bከቴሌኮሙኒኬሽን እስከ ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ስርጭት ያሉ የሕዝብ መገናኛዎች በኢትዮጵያ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ናቸው። ይህም መንግሥት በአጠቃላይ የመገናኛ የልማት አውታሮች ላይ ሙሉ የበላይነቱን መያዙ፤ ግላዊነት እና ሌሎች ግንኙነቶች በግልጽ ለስለላ ምቹ ኾነዋል ማለት ነው። በአንዳንድ አጋጣሚዎች የመንግሥትን የተጠናከረ እና ውስብስብ የስለላ መረብ አልፈው የሚደረጉ ግንኙነቶች ቢኖሩ እንኳ በየመንደሩ ያሉ ቁጥር ሥፍር የሌላቸው ጆሮ ጠቢዎች በኢትዮጵያን ላይ የሚዘሩት ፍርሃት ቀላል አይደለም። ለምሳሌ ያህል አጠቃላይ አገራዊ ስምምነት የተደረሰ በሚመስል መልኩ፤ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ግለሰቦች ድምጻቸውን የሹክሹክታ ያህል አሳንሰው ሲያወሩ ማየት ያልተለመደ አይደለም። በተለይ በመዲናችን አዲስ አበባ የራስ ትከሻን እየተጠራጠሩ ማውራት ወይም በታክሲ እንዲሁም በሻይ ቤቶች ቁጭ ብለው የሚወያዩ ሰዎች አፋቸውን ከልለው ማውራታቸው የአደባባይ ምስጢር ነው። በዚህም አስፈሪ እና ዝግ በኾነ ምህዳር ምክንያት ዜጎች ዝምታን መርጠዋል። ዝምታውም ከቁጥጥራቸው በላይ የኾነውን ስለላ በተቃውሞ መግለጻቸውን ዋነኛ ማሳያ ነው። “ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባም” መሠል አባባሎች አሁን የሚታየውን የፍርሃት ጥግ የሚገልጹ ናቸው።

አጠቃላይ አፈናው ፈርጀ ብዙ ነው፤ መንግሥት ላይ ያላቸው ልዩነት በሰላ ብዕርየሚከትቡትን ጦማሮች እና ድረ ገፆች ያግዳል፣ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ የስለላ ሶፍትዌሮችን በመግዛት በአገር ውስጥም ኾነ ባህር ማዶ ያሉ ዜጎቹን ይሰልላል እንዲሁም ምስጠራን የሚያግዙ መመሪያዎችን ተጠቅማችኋልም ብሎ ጦማሪያንን ያስራል። በአሁኑ ጊዜ የሃሰት ስሞችን ወይም የብዕር ስሞችን መጠቀም ልክ በአደባባይ ሲያወሩ ኋላ እና ፊትን ገልመጥ እያሉ ወይም አፍን ከለል አድርጎ ማውራት ዓይነት በመስመር ላይ ግንኙነት የሚስተዋል ጠባይ ኾኗል። ብዙዎች ማንነታቸውን ለአደጋ የማያጋልጡ የሃሰት ስሞችን ካልተጠቀሙ በስተቀር የማህበራዊ ገጾች ተሳትፏቸው እጅግ ዝቅተኛ ነው። ፖለቲካ ነክ ጉዳዮች ላይ አስተያየት አይሰጡም፣ አያካፍሉም ወይም ማንበባቸውን የሚጠቁም ምልክት አያሳዩም። የመንግሥት ሥርዓት የለሽ ክስ እና እስራት (በርካታ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እንዲሁም የማኅበራዊ ድረገጽ ተጠቃሚዎች ሃሳባቸውን ብቻ በመግለጻቸው በግፍ መታሰር እና መወንጀል) ለብዙሃን ፍርሃት ምክንያት ኾኗል።

ይሁንና ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሉ ችግሩ ውስብስብ ኾኖ ይታያል። የሃሰት ስሞችን ተጠቅሞም በአደባባይ ሃሳብን መግለጽ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች ዋስትና ላይኖረው ይችላል። ለምሳሌ ያህል በአሜሪካ አገር መቀመጫውን ያደረገው የኢትዮጵያዊው የተመሳሳይ ጾታ መብት አቀንቃኝ የፌስቡክ ገጽ ከተጠቃሚዎች በተላኩ በርካታ መልዕክቶች በሚል ሰበብ እንዲዘጋ ተደርጎ ነበር። ፌስቡክ የተላኩለት መልዕክቶች ጥላቻን መሠረት አድርገው የተፈበረኩ መኾናቸውን ተረድቶ ገጹን በመጨረሻ ለባለቤቱ ቢመልስም፤ አጋጥሚው ግን የስውር ስም ወይም ምስጢራዊነትን መጠቀም ብቻውን የመንግሥትን አፋኝነት ጥሶ ለማለፍ በቂ አለመኾኑን አሳይቷል።

ራስን ከስለላ የመከላከያ ብልሃቶች መመሪያ በአማርኛ እንደ መፍትሄ?

ይህንን የስለላ መከላከያ ብልሃቶች መመሪያ ለመተርጎም ሞያዊ እና ግለሰባዊ ምክንያቶች ነበሩኝ። በመጀመሪያ ደረጃ ውስብስብ እና ሕገ-ወጥ የኾነው የስልክ መጥለፍ ስለላ ተጠቂ ነኝ። በ2005 ዓ.ም ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት መንግሥት ስልኬን ጠልፏል። ይህንንም የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ባልደረቦቼን እና ወዳጆቼን ሕጋዊ ባልኾነ መንገድ ለመወንጀል ተጠቅሞበታል። እንዴት የስልክ አገልግሎት ሰጪው ኢትዮቴሌኮም ስልኮች እንዲጠለፉ ለመንግሥት ፍቃዱን ሰጠ ብለው ለሚጠይቁ የዋህ አንባቢዎች መልሱ ግልጽ ነው፤ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ አገልግሎት ሰጪ ሲኾን ያለው ንብረትነቱም የመንግሥት ነው። በዚህም ምክንያት የማንኛውም ግለሰብ የስልክ ግንኑኘት መንግሥት በፈለገው ግዜ ሁሉ ይጠለፋል። ይህ ወደ አማርኛ የተረጎምኩት የስለላ መከላከያ መመሪያ ችግሩን ሁሉ ይቀርፋል ብዬ ባልናገርም፤ የሚልዮኖችን ግላዊነት ለማስጠበቅ ግን አንዱ እርምጃ ነው የሚል ዕምነት አለኝ። በአንድ በስለላ በተከበበ ሥርዓት ውስጥ እንደመኖሬ መጠንም መመሪያውን በአገራችን ቋንቋ ማዘጋጀቱ የእኔም ኃላፊነት እንደኾነ አስባለሁ። ስለዚህም መመሪያውን ወደ አማርኛ መመለሱ በሕይወቱ የስለላን አስከፊነት የተገነዘበ ወይም የሥርዓቱ ሰለባ የኾነ ግለሰብ የሰጠው ምላሽ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ዘወትር በመንግሥት የስለላ መረብ ውስጥ ሌት ተቀን መከራቸው ለሚያዩ ዜጎች የሚደረግ አንዱ የድጋፍ ዘመቻ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል።

በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በዘመነው ዓለም ጥቂት ዓመታትን እንደማስቆጠሬ እራሴን የኢትዮጵያ የዲጂታል ከባቢ “አንትሮፖሎጂስት” አድርጌ እቆጥረዋለሁ። ኢትዮጵያ ለሰዓታት አልፎም ለቀናት የኤሊክትሪክ ኃይል የሚቆረጥባት ስትሆን በርካቶች የኢንተርኔት አገልግሎት ለማግኘት ኢንተርኔት ካፌዎችን የሚያጨናንቁባት አገር ናት። ኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ ሳይበግራቸው ለሰዓታት በኢንተርኔት ካፌ ውስጥ የሚገለገሉ በርካቶች ናቸው። አዲስ አበባ በነበርኩበት ወቅት በመብራት መቆራረጥ ምክንያት ሳይዘጉ የተተዉ የሌሎች ሰዎችን ፌስቡክ እና ኢሜል የመዝጋት ኃላፊነት አጋጣሚዎች ነበሩኝ። ብዙዎች ስለድረገጽ የደህንነት ጉዳዮች በቂ መረጃ እንደሌላቸው ተገንዝብያለሁ። ከአስተዋልኳቸው የተጠቃሚዎች ደካማ የድረገጽ አጠቃቀም ጠባይ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው። የድር ማሰሻውን ድርብርብ በኾነው ማመስጠሪያ አለመጠቀም፣ ለሁሉም የመስመር ላይ ግንኙነት ተመሳሳይ ወይም ደካማ የኾኑ ማለፊያ ቃላትን መጠቀም፣ ደህንነቱ ያልጠረጋገጠ ድረ ገጽ መክፈት፣ ስምምነቶችን እና የደረገጽ ደንቦችን በወጉ ሳያስተውሉ መፈረም እንዲኹም ለሰርጎ ገቦች መረጃን አሳልፎ መስጠት እና የመሳሰሉት። እንደዚህ ዓይነት ስህተቶች ይህን የአማርኛ ትርጉም የበለጠ አስፈላጊ ያደርጉታል። በተጨማሪም ዊኪ ሊኪስ በቅርቡ ኢትዮጵያ ከሃኪንክ ቲም ውድ የኾነ የስለላ ሶፍትዌር መግዛቱን እነደዘገበው ሁሉ መንግሥት ዜጎቹን ለመሰለል ብዙ ገንዘብ ያወጣል እና እንዲህ ዓይነቱ መመሪያ መዘጋጀቱ ጠቀሜታው የጎላ ነው። ይህንን መመሪያ በአማርኛ በማተምም፣ በሚያካሂዳቸው መጠነ ሠፊ የስለላ ወንጀል የኢትዮጵያ መንግሥትን ለፍርድ ለማቅረብ ኢ.ኤፍ.ኤፍ የሚያደርገውን ጥረት ያጎላዋል።

ስለ ትርጉም ሥራው

እራስን ከስለላ የመከላከያ ብልሃቶች መመሪያ ውስብስብ ጉዳይ ነው። ይኹንና መመሪያውን በጥልቀት በማንበብ እና ተግባራዊ ሙከራዎችን በማድረግ የአማርኛው መመሪያ ይበልጥ ተነባቢ እና ቀላል እንዲኾን ጥረት አድርጊያለሁ። ማንኛውም አንባቢ እንደሚረዳው አማርኛችን በቴክኖሎጂ ቃላት የበለጸገ አይደለም። ለምሳሌ ያህል በኢንክሪፕሽን እና በክሪፕቶግራፊ ያለውን ልዩነት በአማርኛ ለማስቀመጥ ይቸግራል። እንዲህ ዓይነት ጉዳይ በሚያጋጥም ወቅትም በአውደ ንባቡ አንባቢ እንዲረዳው ተጨማሪ ማብራሪያ እንድጽፍ አስገድዶኛል። እንዲሁም እንደ ኦፕን ሶርስ፣ ዳታ፣ ሊንክ፣ ዳታ ቢዝ፣ እና ዶሜይን ኔም የመሳሰሉት የቴክኖሎጂ ቃላት ሲያጋጥሙኝ የአማርኛ-ቴክኖሎጂ መዝገበ ቃላት እንዲሁም መደበኛውን የአማርኛ-እንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት በመጠቀም ፍቻቸውን አስቀምጫለሁ። በተጨማሪም “ጌይ” የሚለውን ያለ ምንም ቅጥያ ለማስተዋወቅ ስለፈለግሁ “ሓዋረ ብእሲ” የሚለውን ፍቺ ከዎልፍ ሌስላው ግዕዝ-እንግሊዝኛ መዝገባ ቃላት ተጠቅሚያለሁ። ይህም በኢትዮጵያዊው ጦማር ላይ ተጠቅሶ ይገኛል።

ማጠቃለያ

ግለሰቦች የመስመር ግንኙነታቸውን ደህንነት እንዲጠብቁ ማስተማር አንዱ የግላዊነት መብት ተከራካሪነት ተግባር ነው። መንግሥት እና የሕግ አስፈጻሚው አካል እንደ ሕግ ስለላን ወስደው ዜጎችን በቁጥጥር ውስጥ በሚያስገቡ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ደግሞ አስፈላጊነቱ የጎላ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ስለላ የሚያካሂደው ለዜጎቹ ደህንነት አስቦ እንደኾነ በመከራከል ለማሳመን ይሞክራል። እውነታው ይህ እንዳልኾነ ጸሐይ የሞቀው ጉዳይ ቢኾንም። ይህ የአማርኛ መመሪያ ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲቆዩ ግላዊነትን መመሪያቸው እንዲያደርጉ ይመክራል፤ ያስተምራልም።

Advertisements

ህወሓት ለሽብር ጥቃት ተዘጋጅቷል፤ እንጠንቀቅ

July 24, 2015

def-thumbዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ፣ በሕዝባዊ ኃይሎች ላይ ሊወስድ ያሰበው እርምጃ ተቀባይነት እንዲያገኝለት የሽብር ተግባር ፈጽሞ በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ለማላከክ ወስኗል። እንዲህ ዓይነቱ እኩይ ተግባር ህወሓት ስልጣን ከመያዙ በፊትም በኋላም ሲያደርገው የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ህወሓት እንዲህ ዓይነቱ ኢሰብዓዊና ዘግናኝ ተግባር ለመፈፀም የሚያስችሉ እኩይ ስለልቦና እና ልምድ አለው።

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ በቅርቡ የጀመረው የነፃነት ትግል የፈጠረበት መደናገጥ ለመሸፈንና ንቅናቄውን በኢትዮጵያ ሕዝብና በዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብ ለማስወገዝ ያግዘኛል ብሎ ያመነበት ይህን ዘግናኝ ሴራ ከሳምንት በፊት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁቱን አጠናቆ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ የነፃ ሚዲያ አባላት ደርሰውበት ለሕዝብ ይፋ በማድረጋቸው እንዲዘገይ ተደርጎ ነበር። አሁን በደረሰን መረጃ ደግሞ ሴራው ከበፊቱ በባሰ እና ይበልጥ አውዳሚ በሆነ መጠን ተግባራዊ ለማድረግ የህወሓት “ስውር” መንግሥት ወስኗል። በዚህም ምክንያት ይህ የማስጠንቀቂያ መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በማያሻማ ሁኔታ እንዲገነዘብ የምንፈልገው ሀቅ የሚከተለው ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በደረሰው መረጃ መሠረት ህወሓት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ወስኗል። የእቅዱ ዓላማ ዘግናኝ እርምጃ በንፁሃን ዜጎችና ሕፃናት ላይ በማድረስ “የሽብር ጥቃቶች ሰለባ” ነኝ በማለት የኢትዮጵያ እና የዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ አዘኔታ ማግኘት ነው። የዩ. ኤስ. አሜሪካ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያን የሚጎበኙ መሆኑ ደግሞ ይህንን እቅድ ተግባራዊ የማድረግ ጉጉቱ እንዲጨምር አድርጓል። ስለሆነም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ በህወሓት የሽብር አደጋ ውስጥ ነች። የቦሌ ዓለም ዓቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ እና ወደዚያ የሚያደርሰው መንገድ፣ የአፍሪቃ ኅብረት ጽ/ቤት እና የአሜሪካ ኤምባሲ ህወሓት በሽብር ጥቃት ዒላማነት ከመዘገባቸው ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው።

አርበኞች ግንቦት 7 በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚቃጡ የሽብር ጥቃቶችን መቃወም ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተባብሮ ያመክናል። ይህ በህወሓት የተደገሰልንን የሽብር ጥቃት ማምከን ይኖርብናል። እኩይ እቅድን አስቀድሞ አውቆ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አንድ ዓይነተኛ የሽብር መከላከያ ዘዴ ነው። በዚህ ረገድ በአገዛዙ ውስጥ ያላችሁ የሕዝብ ወገኖች ባለውለታዎች ናችሁ።

የእያንዳንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕይወት መለኪያ በሌለው መጠን ውድና ክቡር ነው። በዚህም ምክንያት እያንዳንዱ ዜጋ የህወሓትን እኩይ ሴራ ተገንዝቦ ራሱን፣ ቤተሰቡንና አካባቢውን ከጥቃት እንዲጠብቅ አርበኞች ግንቦት 7 በጥብቅ ያሳስባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

ሰራዊቱ ለመፈንቅለ መንግስት ሊቋምጥ ይችላል

የኢትዮዽያ መከላከያ ሰራዊት እየፈረጠመ የመጣ የኢኮኖሚ ቅርምት በመጪው ጊዜ ሰራዊቱ የሲቪል አሰተዳደሩን በሰሩ የመዋጥ አልያም በመፈንቅለ መንግስት ገሸሽ የማድረግ ዝንባሌ ሊኖረው ይችላል። ዋዜማ ሬድዮ በጉዳዩ ላይ ተከታታይ ዘገባዎች ታቀርባለች። ቻላቸው ታደሰ ያዘጋጀውን አድምጡ
Audio Player

የኢትዮጵያ ጦር ሃይል በአፍሪካ ከግብፅ ቀጥሎ ሁለተኛው ጠንካራ ሃይል ሲሆን በዓለም ደግሞ 29ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ካሉት አምስት ሃያላን ሀገራት አንዷ ነች፡፡ ለዚህ ደረጃ ያበቃት አንዱና ዋኛው አላባ ወታደራዊ ሃይሏ ነው፡፡ ጦር ሰራዊቱ ከአሜሪካ መንግስትም ወታደራዊ እርዳታ ሲቸረው እንደኖረ ይታወቃል፡፡ ለሀገሪቱ በአፍሪካ ቀንድ ልዕለ ሃያል ሀገር (regional hegemon) መሆን መንግስትና አንዳንድ ታዛቢዎች አስረጂ አድርገው የሚያቀርቡትም ወታደራዊ ሃይሏ ነው፡፡
መንግስትም ሰራዊቱ የሀገሪቱ ሉዓላዊነት ጠባቂ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ ከውጭ የምታስገባቸውን የውጭ ምርቶች በሀገር ውስጥ በማምረት የቴክኖሎጂ ሽግግር ዋልታ፣ የኢትዮጵያ ትንሳዔ አብሳሪና የኢኮኖሚ ዕድገቱ ምሰሶ መሆኑን ደጋግሞ ይገልፃል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁንም ቢሆን ወታደራዊ-ነክ ጉዳዮች በህዝቡም ሆነ በተቃዋሚዎች ዘንድ በአደባባይ ውይይት የማይደረግባቸው አይነኬ ጉዳዮች በመሆናቸው ህዝቡ በቂ ግንዛቤ የለውም፡፡ የመከላከያ ኢንዱስትሪው ግዙፍ ሃብትና ምርቶች በከፊልም ቢሆን ለህዝቡ ይፋ የሆኑት በከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየዓመቱ በሚከበሩት የሰራዊቱ ቀኖች ወቅት በተዘጋጁት ኤግዚብሽኖች አማካኝነት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ስለሆነም ከግዙፉ ወታደራዊ ኢንዱስትሪ ጀርባ የሚያንዣብበው ፖለቲካዊ አደጋ ገና በደንብ የተጤነ አይመስልም፡፡ በመከላከያ ሚንስቴር ሚስጢራዊነት ሳቢያም በወታደራዊ ኢንዱስትሪው ባጀት አጠቃቀምም ሆነ የሰራ ሂደቱ ላይ ፓርላማው ያለው ቁጥጥር በጣም አነስተኛ እንደሆነ የሚካድ አይደለም፡፡
ባለፉት ጥቂት ዓመታት መንግስት ለጦር ሰራዊቱ የኢኮኖሚ አቅም መጎልበት የሰጠው ትኩረት በማደጉ በህግ ማዕቀፍ ረገድ የጦር ሰራዊቱ ኢኮኖሚያዊ ይዞታ እንዲፈረጥም የሚያስችሉ ደንቦችንና አዋጆችን በማውጣት በስራ ላይ አውሏል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ በመንግስት ልማት ድርጅትነት የተመዘገቡት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ፣ የመከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት እንዲሁም የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያ ደንቦች ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የሰራዊቱን ሞራልና ኑሮ ለማሻሻል ያስችላል የተባለው የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽንም በህግ ተፈቅዶ ሰራ ላይ ውሏል፡፡
በተለይ ከአምስት ዓመት በፊት በ10 ቢሊዮን ብር (ወይም ግማሽ ሚሊዮን ዶላር) መነሻ ካፒታል የተቋቋመው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የተላለፉለትን የልማት ድርጅቶች ጨምሮ የ15 ግዙፍ ኢንዱስትሪዎችና የ100 ፋብሪካዎች ባለቤት ሆኗል፡፡ የተሽከርካሪ መገጣጠሚያና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች ብቻ በዓመት ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስገቡ የቅርብ ጊዜ ሪፖርቶች ይጠቅሳሉ፡፡
በአሁኑ ጊዜ የመከላከያ ወታደራዊ ኢንዱስትሪ ያልገባበት ትርፋማ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ማግኘት አዳጋች እየሆነ ነው፡፡ በወታደራዊ ፍጆታዎች በኩልም አውቶማቲክ መሳሪያዎች፣ የታንክ መለዋወጫዎች፣ ሞርታርና ላውንቸር የሚያመርት ሲሆን ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችንና አውሮፕላኖችንም የመጠገን አቅም አዳብሯል፡፡
የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች “ተልዕኳቸውን ለማሳካት በሚያስችሉ ዘርፎች” ሁሉ እንዲሰማሩ መንግስት ስለፈቀደላቸው እምብዛም ገደብ የለባቸውም፡፡ ስለሆነም ድርጅቶቹ ለሲቪል አገልግሎት የሚውል ብረታ ብረት፣ ጀነሬትርና ትራንስፎርመር፣ ከባድ ማሽነሪዎች እንዲሁም የከተማ አውቶብስ፣ የባቡር ፉርጎ፣ ትራክተር፣ ቡል ዶዘርና ተሽከርካሪዎችን የመገጣጠምና ለገበያ ማቅረብም ዋነኛ ስራዎቻቸቸው ሁነዋል፡፡ ከሶስት ዓመት በፊትም መከላከያ ሚንስቴር “የሰራዊት ባንክ” (Army Bank) በማቋቋም ወደ ፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለመግባት እያቆበቆበ ስለመሆኑ ለፓርላማው ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
መንግስትም አሁንም በርካታ ግዙፍ የግንባታ ፕሮጄክቶችንና ምርት አቅርቦቶችን ያለ ጨረታ ለመከላከያ ተቋማት በኮንትራት እየሰጠ ይገኛል፡፡ የተቋሙ ኢንዱስትሪዎች የታላቁ ህዳሴ ግድብን ኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች ከመረከባቸውም በላይ በአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የተያዙትን በርካታ የስኳር ልማትና ማዳበሪያ ፕሮጄከቶችንም እየገነቡ ይገኛሉ፡፡
እዚህ ላይ አሳዛኙ ነገር የሀገሪቱ የግል ዘርፍ ከወታደራዊ ኢንዱስትሪው ጋር ሽርክና የሌለው መሆኑ ነው፡፡ በአንፃሩ የመከላከያው ኢንዱስትሪ ተቋማት ዋነኛ ሸሪኮች መሰል የአሜሪካ፣ አውሮፓና ቻይና ድርጅቶች ብቻ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ኢንዱስትሪዎቹ ከሃያላን ሀገሮች ጦር መሳሪያ አምራች ድርጅቶች ጋር ብቻ ሳይሆን በተባበሩት መንግስታት የጦር መሳሪያ ማዕቅብ ከተጣለባት ሰሜን ኮሪያ ጋር ሳይቀር የስራ ግንኙነት እንዳላቸው ሪፖርቶች ይጠቁማሉ፡፡
ገና በማቆጠቆጥ ላይ ካለው የሀገሪቱ ኢንዱስትሪ አንፃር ሲታይ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በበላይነትና ምናልባትም በብቸኝነት ለመቆጣጠር በመንደርደር ላይ መሆኑን ያሳያል፡፡ በዚህ ላይ የህወሃት ኢንዶውመንቶች ሲታከሉበት በነፃ ገበያ ላይ የተመሰረተው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከሁለት አቅጣጫ ከባድ አደጋ እንደተደቀነበት ያረጋግጣል፡፡ ስለሆነም የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኢምፓዬር በግዙፎቹ የህወሃት ኢንዶውመንቶች ተደቁሰው በመቀጨጭ ላይ ያሉትን የግል ድርጅቶች ጭራሹን ከገበያ እንዳያሳወጣቸው ያሰጋል፡፡ ምናልባት ህወሃት ኢንዶውመንቶቹ ከመከላከያ ኢንዱስትሪዎች ጋር የሚዋሃዱበት ወይም በጋራ የሚሰሩበትን ዕድል ያመቻች ይሆናል እንጂ የመከላከያ ኢንዱስትሪዎች ወደፊት ከኢንዶውመንቶች ጋርም ፉክክር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡
ሁኔታውን በቅርብ የሚከታተሉ ታዛቢዎች እንደሚሉት የጦር ሰራዊቱ ኢኮኖሚያዊ ጡንቻ መፈርጠም በሀገሪቱ ፖለቲካ ላይ ቁልፍ ሚና እንዲኖረው መገፋፋታቸው አይቀሬ ይሆናል ይላሉ፡፡ እንዲያውም የአንዳንድ ታዛቢዎች ስጋት በጦር ሰራዊቱ የሚቀነባበር ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስትንም የሚጨምር ሁኗል፡፡
አሁን ዋናው ጥያቄ ይህ የወታደራዊ ኢኮኖሚያዊ ጡንቻ መፈርጠም ምን ዓይነት ፖለቲካዊና ወታደራዊ ውጤት ያስከትላል? የሚለው ይሆናል፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ሁለት ተፎካካሪ የስልጣን ማዕከሎች (contending power centers) ይፈጠሩ ይሆን? እውነት አንዳንድ ታዛቢዎች እንደሚሰጉት ሁኔታው አንፃራዊ ነፃነት በመጎናፀፍ ላይ ያለው የጦር ሰራዊቱ አመራር ለሲቪሉ መንግስት ያለው ተጠያቂነት ላልቶ ጦር ሰራዊቱ ራሱ የፖለቲካ ተዋናይ እንዲሆንና ስልጣን እንዲይዝ ያደርገው ይሆን? የሚሉትን ጥያቄዎች መፈተሽ ተገቢ ነው፡፡
ኢትዮጵያን የእጅ መዳፋቸውን ያህል ያውቋታል የሚባልላቸው ታዋቂው አሜሪካዊ ምሁር ሬኒ ሌፎርት አምና ባስነበቡት አንድ መጣጥፍ “የፀጥታ ሃይሎችና ጦር ሰራዊቱ በመንግስት ውስጥ ያለ ሌላ መንግስት (a state within a state)” ሁነዋል እስከማለት ደርሰዋል፡፡ ተጠሪነታቸውም ለሲቪሉ መንግስት ሳይሆን ለራሳቸውና ለተወሰኑ የህወሃት አመራሮች ብቻ መሆኑንም በመጠቆም፡፡ “በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ፖለቲካ በጠመንጃ ላይ የነበረውን የበላይነት አጥቷል” ሲሉ መደምደማቸውም የሀገራችን ሁኔታ ምን ያህል አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ይጠቁማል፡፡
የምሁሩ ከባድ ድምዳሜዎች ሀገሪቱ ለወታደራዊ አገዛዝ ወይም መፈንቅለ መንግስት የተመቻቸ ሁኔታ ላይ እንደሆነች የሚያረጋግጡ ናቸው፡፡ በአንፃሩ ግን በህገ-መንግስቱ መሰረት ጠቅላይ ሚንስትሩ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መሆናቸውን ለሚያውቀው ተራው የኢትዮጰያ ህዝብ አስደንጋጭ መርዶ መሆናቸው እሙን ነው፡፡
በእርግጥ እስካሁን ያለው ሁኔታ ምሁሩ ሬኒ ሌፎርት የገለጡትን ያህል ስለመሆኑ ሊያጠራጥር ይችል ይሆናል፡፡ ሆኖም ሁኔታዎች በዚሁ ከቀጠሉ ዜጎች አንድ ቀን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ሀገራቸውን በይፋዊ ወታደራዊ መዳፍ ስር ላለማግኘታቸው ዋስትና የለም፡፡ እንደሚታወቀው በአፍሪካ የግዙፍ ወታደራዊና ሲቪል ኢንዱስትሪዎች ባለቤት በመሆን ረገድ ዋነኛ ተጠቃሽ የሆነው የግብፅ ጦር ሰራዊት የዕለት ተለት ምግብ ፍጆታ የሆነውን ዳቦ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ሳይቀር ባለቤት መሆኑ ምን ያህል ዋነኛ የፖለቲካ ተዋናይ እንዳደረገው ባለፉት አራት ዓመታት በገሃድ እየታየ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ጦር ሃይል በፖለቲካው ላይ ስለሚኖረው ሚና ሶስት ዋና ዋና የ“ቢሆን መላ ምቶች”ን (possible scenarios) ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
አንደኛው መላ ምት ሲቪሉ መንግስት ህገ መንግስቱን በመጣስ ጦር ሰራዊቱ የሀገር ውስጥ ፖለቲካው የጀርባ አጥንት እንዲሆን ሁኔታዎችን ሊያመቻች ይችላል የሚለው ነው፡፡ ሰራዊቱም የቢዘነስ ኢምፓዬር እንዲገነባ የፈቀደለት የፖለቲካ ስርዓት በማናቸውም መልኩ እንዲቀጥል ጥብቅና በመቆም የሁለትዮሽ እከክልኝ ልከክልህ አሰራር እንዲሰፍን ሊያደርግ ይችላል፡፡ በሌላ አነጋገር ሲቪሉ መንግስት ሲቪላዊ ማንነቱንና አደረጃጀቱን ይዞ እንዲቀጥል ለማስቻል ጦር ሰራዊቱ ሃይል እስከመጠቀም ሊደርስ ይችላል፡፡ ወይም መፈንቅለ መንግስትን እንደ ማስፈራሪያ በመጠቀም በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት እንዲቀጥል ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡ በግብፅ ከዓመታት በፊት ሆስኒ ሙባረክ በህዝባዊ ተቃውሞና በራሱ በጦር ሰራዊቱ የመጨረሻ ሰዓት ግፊት ከስልጣን እስኪወርዱ ድረስ ጦር ሃይሉ ምንጊዜም የሲቪሉ መንግስት ጠበቃ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
ከጅምሩም የሀገራችን ጦር ሰራዊት ፖለቲካዊ ገለልተኛነት አስተማማኝ ባይሆንም ሲቪሉ መንግስታዊ አመራር የጦር ሰራዊቱ መኮንኖች በፖለቲካ ውስጥ እንዲገቡ ጥርጊያ መንገዱን ያመቻቸላቸው ግን እኤአ ከ2001 የህወሃት ክፍፍል ጀምሮ ነው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ስለሆነም የጦር ሰራዊቱ አመራርና የሲቪሉ ፖለቲካዊ አመራር እጅና ጓንት መሆን ይህን የ“ቢሆን መላ ምት” ከመላ ምትነት አልፎ ወደ ተጨባጭነት የተጠጋ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ በእርግጥ እስካሁንም ከሞላ ጎደል በተግባር ሲታይ የኖረው ይህንኑ የሚያጠናክር ነው ማለት ይቻላል፡፡
ሁለተኛው የ“ቢሆን መላ ምት” ደግሞ በሲቪሉ አመራርና ወታደሩ የስልጣን ሽኩቻ ተነስቶ ሰራዊቱ ሲቪሉን መንግስት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ገልብጦ ስልጣን ሊይዝ ይችላል የሚለው ነው፡፡ ልክ ከዓመት በፊት ታይላንድ በፖለቲካዊ ችግር ውስጥ ስትዘፈቅ ጦር ሰራዊቱ እንዳደረገው መፈንቅለ መንግስት ወይም ከዓመት በፊት የግብፅ ጦር ሰራዊት በዴሞክራሲያዊ መንገድ ፕሬዝዳንት ሆነው በተመረጡት የሙስሊም ወንድማማቾቹ ሙሃመድ ሙርሲ ላይ እንዳደረገው መፈንቅለ መንግስት ዓይነት ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ይኸኛው የ“ቢሆን መላ ምት” በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በአጭርና መካከለኛ ጊዜ ውስጥ የመሞከሩም ሆነ የመሳካት ዕድሉ እምብዛም ይመስላል፡፡
በሶሰተኛ ደረጃ ሊጠቀስ የሚችለው የ“ቢሆን መላ ምት” ጦር ሰራዊቱ በሲቭሉ መንግስት ጋባዥነት (coup with civilian consent) በብቸኝነት ወይም ከራሱ ከሲቪሉ ጋር ተዳብሎ ስልጣን ሊይዝ ይችላል የሚለው ነው፡፡ በእርግጥም እስካሁን የሚታየው የህወሃት-ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ሁኔታ እንደ የመጀመሪያው መላ ምት ሁሉ ይህንንም መላ ምት የሚያጠናክር ይመስላል፡፡ ስለሆነም ከመፈንቅለ መንግስት አንፃር ከታየ ለእውነታ የሚቀርበው ይኸኛው ነው፡፡
በጠቅላላው እንዲህ ዓይነቶቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ገፊ ምክንያቶች ሊሆኑ ከሚችሉት ውስጥ ዋነኛው መጠነ-ሰፊ ሀገራዊ ፖለቲካዊ ቀውስ መከሰት እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ለምሳሌ እንደ 1997ቱ ምርጫ-አመጣሽ ቀውስ ዓይነት፡፡ ፖለቲካዊ ቀውስ የሚፈጠረው ደግሞ ኢህአዴግ-መራሹ መንግስት ለሀገሪቱ ፖለቲካዊ ችግሮች ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ መስጠት ካቻለ ወይም ካፈለገ ይሆናል፡፡ መላ ምቱ ለእውነታ ያለውን ቅርበት የሚያሳየው ደግሞ መንግስት ለሀገሪቱ ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ያለው ፖለቲካዊ ፍላጎትና ተቋማዊ ብቃት እየተኮላሽ መሄዱ ነው፡፡

ጥብቅ መልእክትና ማሳሰቢያ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ( አርበኞች ግንቦት ሰባትና ደህሚት ሰራዊት)

የአርበኞች ግንቦት ሰባትና ደህሚት ሰራዊት ዉድ የሆነችዉን ህይወታቸዉን ከፍላዉ ኢትዮጵያን ከዘረኛዉ፤ከከፋፋዪ፤ እዉነትና እዉቀት ከራቃቸዉ ጥቂት የባነዳ ልጆች ነፃ ለማዉጣትና የተከበረች፤ የተፈራች፤ ለዜጎቿ ምቹ የሆነች፤ ሁሎም ልጆቿ የሚቧርቁባትንና የሚበለፅጉባትን ኢትዮጵያን ለመመስረት ትግሉን መጀመሩን የሰማችሁ ይመስለናል፡፡ አገር ቤት ላለዉ ዘመዶቻችን መልእክቱን ንገሩ፡፡
በአርነኞች ግንቦት 7 አባል የማስተላልፈዉ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ የሚከተለዉን ይመስላል፡፡

1. በ ሚያዚያ ወር 2007 ዓም ወያኔ የግል የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንዳካሄደ ይታወቃል፡፡ ይህን መሰረት አድርጎ በወያኔ ሎሌወችና ባንዳዎች መሰረት መሳሪያህን ሊያስወርድህ እንደሆነ ሰሞኑን ከአገኘሁት የደህንነት ሚስጥር አካፍልሀለሁ፡፡ ባነዳወችን በጥንቃቄ ተከታተል፡፡ ኢትዮጵያዊ ዋናዉ ጀግንነቱ ርስቱና ነፃነቱ የሆነችዉን የጦር መሳሪያዉን ለማንም ባንዳ የሚያስረክብ ስነ-ልቦና እንደሌላዉ ታሪካችን ያስረዳልና የታሪክ ተወቃሽ እንዳትሆኑ ንቁና ባንዳዎችን ተከታተሉ፡፡ ማንንም የወያኔ ባንዳ እንዳታምኑ፡፡ መሳሪያህን ሊያስወርድ ከሞከረ በቡድን ሁነህ ለነፃነትህ ሸፍት ፡፡ የወያኔ ሰራዊትን በቡድን ሁነህ በማጥቃት መሳሪያዉን ተረከብ ነገር ግን የወንድምህን ህይወት በከንቱ እንዳትቀጥፍ ተጠንቀቅ፡፡ ቤት ያፈራዉን መግበዉ ልብስም አልብሰዉ፡፡ የነፃነት ታጋዮችን እንዲቀላቀልም መንገድ ምራዉ፡፡

2. የወያኔ ቁጥር አንድ ተላላኪ ባንዳ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጦርነቱን ከወንድማችንና ከእህታችን የኤርትራ መንግስትና ህዝብ ነዉ ሲል 100 ፐርሰንት የግሉ ባደረገዉ የዝንጀሮዉ ምክርቤት ጋር መምከሩን በ ኢትዮጵያ ስም በሚነግድበት ቴሌቪዝንና ሬድዮ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ይህ የተለመደ ቀልድ ነዉ፡፡ ይህ የነፃነት ጦርነት 100 ፐርሰንት የምርጫ ካርዱን ከ 1997 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ምርጫ በተዘረፈዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆችና ጥቂት በስርአቱ የበለፀጉና የህዝብን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸዉ ካደረጉ ወያኔዎች፤ባንዳዎችና ተላላኪዎች መካከል እንጂ ከ ኤርትራ ህዝብና መንግስት ጋር አይደለም፡፡ የኤርትራን ህዝብ ሞክሩት እኛም ከጎናቸዉ እንሆናለን፡፡ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የቀለዳችሁብንን አንረሳዉም፡፡ የባድመ መሬት ሲወረር ሉአላዊ ግዘተችን ተወረረ ብላችሁ የጎንደር ድንበርን መሬት ለሱዳን ሰጥታችሁ ቁራጭ መሬት እያላችሁ መቀለዳችሁን አትርሱት፡፡ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ብትጨነቁ ሱዳን ላይ እንዝመት ትሉን ነበር፡፡

3. በአንዳን ከተሞች የትግራይን ህዝብ ይሁንታ ለማግኘት በግንቦት ሰባትና በሌላዉ ብሄር ስም ( በተለይም በአማራዉ) ወያኔ በትግረኛ ተናጋሪዎች ድርጅትና ነብስ በድብቅ በመግደልና ድርጅታቸዉን በቦንብ በማፈራረስ የትግራይ ህዝብ እንዲነሳና ሌላዉም ህዝብ ይህን እኩይ ተግባር በመኮነን ከነፃነት ታጋዮች እንዳይሰለፍ የተለመደ በሀዉዜን ህዝብ ላይ የሰራዉን ሴራ ሊሰራ መዘጋጀቱንና የዶኪመንተሪ ፊልምም ሊሰሩ ስለተዘጋጁ የትግይ ተወላጅ የሆናችሁና በሌላዉ ክልልና በትግራይ የምትኖሩ ትግረኛ ተናጋሪወች ጥንቃቄ እንድታደርጉ አደራ እንላለን፡፡ ወያኔ መቸዉንም ቢሆን መጀመሪያ የሚነግደዉ በእናንተ ደምና ስም ነዉ፡፡ ሌላዉም ብሄር በወያኔ ፕሮፖጋንዳ የደነዘዛችሁ በወንድሞቻችሁንና በእህቶቻችሁን ላይ ምንም አይነት እርምጃ እንዳትወስዱ አደራ እያልን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከማኝኛዉም ጥቃት እንድትጠብቁና ኢትዮጵያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን፡፡

4. ወያኔ ሰሞኑን ዉድ የኢትዮጵያ ልጆችን ለዚህ ቅዱስ ጦርነት በየቀበሌዉ ማስታወቂያ ለጥፎ እየመለመለ ወደ ስልጠና ጣቢያዎች ከማስገባቱም በላይ አምስት ወር ያለሞላቸዉን ሰልጣኞችን ወደ ግንባር እያመላለሰ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ልጆችህን ለዚህ የሰይጣን አማልክት ለሚከተሉ የባንዳ ልጆች እንዳትልክ ማስገንዘብ እንፈልጋልን፡፡ ግንባር ላይ ላለዉ ልጅህም መሳሪያዉን ወደ ባንዳዎች እንዲያዞር መልክት ላክ፡፡

5. ተደራጅታችሁ በሲቪል መስሪያ ቤቶችና በግል ተቋማት ዘረፋ ሊካሄድ ስለሚችል ባንኮችን፤ ሆቴሎችን፤ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ከዘረፋ ጠብቁ፡፡ ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን ቤታችሁ ዉስጥ ችግር እንዳይኖር የምትመገቡትን አዘጋጁ፡፡ የደርግ መንድስት ሲወድቅ የትምህርት ቤት ወንበርና ጠረጴዛ የሀክምና ተቋማት ቁሳቁስ ሳይቀር መዘረፉን እንዳትረሳ፡፡ አገራችንን ከዜሮ መጀመር ሸክሙ ለእኛዉ ነዉ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

ወያኔ ሆይ የባሩዱ ሽታ ይሽተታችሁ!!!!!

መርጋ ደጀኔ  ከ- ኖርዌይ

ወያኔን ከማስተማር አህያን ማስተማር ይቀላል። ምክንያቱም ሂጂ ሲሏት ትሄዳለች ቁሚ ሲሏት ትቆማለች ዙሪ ሲላትም ትዞራለች ወያኔዎች ግን እኛን የሚያቆመን የለም እኛን የሚያዞረን የለም ብለው ደደብነታቸውን በደደብ መሪዎቻቸው እየተናገሩ ኢትዮጵያ ላይ መቀለድ ከጀመሩ 24 ዓመት አለፋቸው። በጣም ስልችት የሚል ቃልና ማንም ኢትዮጵያዊ ያልተቀበላቸው የይስሙላ ቃላቶች በመደርደር እኩልነትን ኢህአዴግ ነው ያመጣው፤ ልማትን ኢህአዴግ ያመጣው ፤ዕድገትን ኢህአዴግ ያመጣው ወ.ዘ.ተ. ወያኔ ያመጣውን የብሔር እኩልነትን ስንፈትሽ በሰላም አቅጣጫ 90% በላይ ቅድምያ የሚሰጠውና ስልጣን የሚያገኘው በየትኛውም ዘርፍ ትግሬ ነው፣ተሰሩ የተባሉትም ፎቆችና ፋብሪካዎችንም ስንቃኝ 90%የወያኔ ሰዎች ናቸው እኩልነት የሚሉት እኩልነት ትግሬኛ ቌንቌ እንደ ማስፈራሪያ እንደመጠቀምያ የደረሰው የወያኔ ቡድን የሚናገረውን በሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደማይቀበለውና ነገር ግን የሚሰማውን የወያኔ ውሸቶች ከመሰልቸቱ አልፎ የሚያናድድ የደደቦች ንግግር መሆኑን ተረድታል። ከዚህ ቀደም ባሩዱን የሚያስጨሱት እነርሱ ነበሩ፣ መቼስ የወያኔ ባሩድ ያልጨሰበት የኢትዮጵያ ግዛት አለ ብሎ ለመናገር ይከብዳል ፣ሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በወያኔ ባሩድ የተጎዱ ናቸው፣ቢመከር ቢዘከር  አልመለስ ያለው ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ታግሶ ታግሶ ወያኔዎችን ባሩዱን ሊያሸታቸው በወኔና በሙሉ ልበኝነት የነጻነት ታጋዮች አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔዎች ላይ ባሩዱን ማሽተት ጀምራል፣ በመጀመሪያ የባሩድ ሽታ ላይ ወያኔዎችን ያስደነገጠ እና ያሸበረ ባሩድ በመልቀቅ ቀላል የማይባል የወያኔ ቅጥረኛ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል። ትንቅንቅ ተጀምራል በወያኔዎች መንደር ድንጋጤ ነግሳል ፣የውስጥ ግጭትም አይሏል መክፋፈል ቀጥላል ወታደሩም በሙሉ ልቡ የመታገል ወኔው ጠፍታል፣ በአሁኑ ሰዓት የወያኔ ሀይል ሆኖ እያገለገለ ያለው የወያኔ ሚዲያ የሆነው ETV,ብቻ ነው፣በETVየውሸት ዲስኩር ይደሰኩራሉ እውነቱ ግን ከፍለፊታቸው መጥታል የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ለመቀበልና  ከጎን እንዳልሆነ ስለሚያውቁ ድንጋጤ ውስጥ ናቸው ። የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ሀይልም ደግሞ 100% በሙሉ ልብ የሚታገሉ በሙሉ ልብ ወያኔን ለመደምሰስ የቆረጡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ነጻነት የቆሙ የህዝብ ድጋፍ ያላቸው የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፥ እንግዲህ ወያኔ ሆይ ባሩዱ ይድረሳችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ በየቤቱ አኴኩታችሁ እንዳሰቃያችሁት በመደሩም ሄዳችሁ እንደገደላቹሁት ያ መከራና  ሞት፤ እንግልትና እስራት፤ ስደትና ረሃብ፤ አንተም ደጃፍ መጥቷል። ትግስት ፍራቻ የመሰላችሁ፤ ዝምታ ሞኝነት ያረጋችሁ፤ እናንተን ለመቅበር የኢትዮጵያን ነጻ አውጭዎች ተነስተዋል። የክፋትን ጉድጋድ አርቀህ አትቆፍረው ምክንያቱም አንተ ልትገባበት ትችላለህ የሚባለው ለዚህ ነው አሁን የት ተደብቃችሁ እንደምታመልጡ እናያለን የትኛው ህብረተሰብ መሀል ገብታችሁ መኖር እንደምትችሉ እንመለከታለን በቌንቌ ማስፈራራት የጀመርክ በሙሉ በቌንቌ የሰውን ህይወት ያጠፋህ በሙሉ ስልጣንህን በመጠቀም ጉዳት ያደረሰ ነገ በሙሉ ነጻነቱን በማወጅ ብድራቱን ለመመለስ ወገኔ ተነስታል የባሩዱንም ሽታ ማሽተቱን ጀምራል፣በፍቅር መማር ካልቻላችሁ መከራው እራሱ ያስተምራችሃል በሰላም ህዝብን ማኖር ካልቻላችሁ ሰላም ናፋቂው ህዝብ ያጠፋችሃል። ውድ የኢትዮጵያ ልጆች ከወያኔ ጉያ በፍጥነት ውጡ ወያኔ ውስጥ ሆናችሁ የወያኔ አገልጋይ የሆናችሁ ከዚህ አገር አጥፊ ጋር ቆማችሁ ሁለተኛ ሞት እንዳትሞት በፍጥነት ውጡ ውድ የመከላከያ ሰራዊት ወያኔ እየሰራ ያለውን ሁላችሁም ታውቁታላችሁ ከራሱ ወገን ውጭ ለሌላው ኢትዮጵያዊ ምንም ግድ እንደሌላቸው ኢትዮጵያን እያጠፋ እንደሆነ ሁሉም የመከለከያ ሰራዊት በደንብ ጠንቅቆ ያውቃል በኢትዮጵያዊያኑ በስተጀርባ ሌላ የነሱ ሰላይ ወይም ሃላፊ  ያለ አግባብ እንደሚያዝህ ታውቃለህ በሌላው ኢትዮጵያዊ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ፈጽሞ ምንም አይነት እምነት እንደሌላቸው ታውቀዋለህ ። እንግዲህም እናተም ከወያኔ ግዛት ነጻ ወጣችሁ በነጻነት በሀገራችሁ የምትሰሩበት ስራዓትን በማምጣት ከፍተኛ ድርሻችሁን ተወጣችሁ ኢትዮጵያን በማዳን ስራ ላይና ዲሞክራሲያዊ ሀገር ግንባታ ላይ ትሳተፉ ዘንድ ግድ ይላችሃል፣ሌላው ህብረተሰብ ከወያኔ ጉያ በመውጣት ወያኔን አጋልጦ በመስጠትና በማጥፋት ስራ ላይ በመሳተፍ ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ወያኔን ደምስሰን የምንኖርበት ሀገር እንዲኖረን ሁሉም የበኩሉን መወጣት አለበት። ወያኔዎች ከእንግዲህ በሃላ የኢትዮጵያ እናትና አባቶች ልጆቻቸው በወያኔ ተገለው ልጄ ልጄ ብለው አያለቅሱም ፣ልጆችም እናቴና አባቴን ብለው አያለቅሱም፣የኢትዮጵያ ህዝብ 24 ዓመት ሙሉ ስትገሉና ስታሰቃዩ ትለወጣላችሁ ብሎ በትግስት ዝም ብሎ ነበር አሁን ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ከወያኔ መልካም ነገር ያስባሉ ማለት ጥቁር ድንጋይ ላይ ውሀ አፍስሶ ወደ ውስጥ ይገባል ብሎ እንደመጠበቅ መሆኑን ተረድቷል። አሁን ግዜው ይቀየራል የመከራው ዘመን ወደ እናንተ ይዞራል የባራዱ ጭስ ወያኔዎች ላይ ይጨሳል ኢትዮጵያዊ ሲያለቅስ ወያኔውና ደጋፊው የሳቁት ሁላ አሁን ተራው ልጄን ልጄን አባት እናቴን ብሎ የማልቀሱ የናንተ ይሆናል ግዜውን ጠብቆ ሁሉም የስራውን ግፍ የእጁን እንደሚያገኝ የታወቀ ነው፣የዘራችሁትን የግፍ ዘር በየተራ ታጭዱታላችሁ ሞት ለዘረኛው ወያኔ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!! – See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44867#sthash.VEi4jACw.o8cYYsAE.dpuf

አርበኞች ግንቦት 7… እየመጡ ነው! አርበኞች ግንቦት 7… አዲስ አበባ ድረስ ሊመጡልህ አይደለም ወይ…

ሰሞኑን ወያኔ እየደለቀው የሚገኘው “የጦርነት ክተት አዋጅ” አታሞ ለጆሯችን አዲስ አይደለም፡፡ የተለመደ ከተራና ትርጉምየለሽ የፖለቲካዊና ወታደራዊ ፕሮፖጋንዳ ያላለፈ ፍርሃት ከወለደው ጭንቀት የመነጨ ቅዠት /Nightmare/ የእንቅልፍ ዓለም እንቅስቃሴ /Somnambulism/ ነው፡፡ ህ.ወ.ሓ.ት ጠብመንጃና ጥይት እንጂ የመዋጋት ስነ-ልቦና ፈፅሞ በውስጡ የሌለውን መከላከያ ሰራዊቱን ቢያንስ፣ ቢያንስ በየስድት ወሩ ወደ ኤርትራና ሱዳን ድንበሮች የስጠጋል፣ መልሶ ያሸሻል ያስጠጋል መልሶ ያሸሻል፡፡ በኦጋዴን በኩልም ከኦብነግና አልሸባብ ጋር በተያያዘ እንዲሁ ነው፡፡ አራቱን የሂሳብ ስሌቶች እንኳን ጠንቅቀው የማያውቁት የወታደራዊ ሳይንስ ሽፍታ “ጨዋ” የህ.ወ.ሓ.ት ጀነራሎች ተግባራቸው ሁሉ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ከሆነ ከራርሟል፡፡ ሟች በሌለበት ገዳይ መሆናቸው እና የሚገባላቸው አያገኙም እንጂ ወጣቶችን በሀገር መከላከያ ስም ለስልጣናቸው እድሜ ማራዘሚያ ለመመልመል ማስታወቂያ ማውጣታቸውም ቢሆን ከዚህ በፊት እየተደጋገመ ያሰለቸን ጉዳይ ነው፡፡

ወያኔዎች እንደ ከዚህ ቀደሙ ዛሬም ወደፊትም አይዋጉም፡፡ በ1991 ዓ.ምና በ92 ዓ.ም የተዋጋው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ በትንሹ ከ100 ሺህ በላይ የድሀ ልጆች በከንቱ ረግፈው ቀርተዋል፡፡ ድሉ ግን የወያኔዎች ብቻ ነበር፡፡ አሁንም ቢሆን የወያኔዎ ዕቅድና ፍላጎት ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ሽማግሌው ስብሃት ነጋ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ የትግርኛ ፕሮግራም “የኤርትራ ጉዳይ ያስተዳደር እንጂ የቅኝ ግዛት አይደልም…” በማለት ከ40 ዓመታት በኋላ ድርጅታቸው ህ.ወ.ሓ.ት አቋሙን መለወጡን ማስታወቃቸው፤ በተጨማሪም ወያኔ-ኢህአዴግ ለምርጫ ቅስቀሳ በየጊዜው የሚለቃቸው ዶክመንተሪዎች የአድዋን ድልና ሌሎችን የህዝቡን ስነ-ልቦና ማስተሳሰሪያ ጠንካራ የታሪክ ክሮች እየመዘዘ ማሳየቱ ከዛሬ 14 እና 15 ዓመታት በፊት እንደሆነው ህዝቡን ለጦርነት በማነሳሳት የድሃ ልጅ የሆኑ ወጣቶችን ደመራ በማድረግ ዳር ሆነው ለመሞቅ ነው፡፡ የሰሞኑ ፕሮፖጋንዳቸው ንፋስ ትክክለኛ አቅጣጫ ይሄ ነው፡፡ ነገር ግን በጠብመንጃ አስገድደው አፉን በማስከፈት የግፍ ገፈት እየጋቱት የሚገኘውን መከረኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ልክ እንደበፊቱ ዛሬም በቀላሉ ማታለል እንደማይቻል ልቦናቸው ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡

ወያኔ ፈለገም አልፈለገም ጦርነቱ አይቀሬ ነው፡፡ ህዝቡ ራሱን መጠየቅና መልስ መስጠት ያለበት ቁምነገር ቢኖር ወያኔ ጦርነት የሚገጥመው ከነማን ጋር ነው? የሚለውን ነው፡፡ ወያኔ በጥሩንባ እንደሚያስለፍፈው ጦርነቱ የምር ከኤርትራ ጋር አይደለም፡፡ ኤርትራ ውስጥና በኤርትራ ዙሪያ በሚገኙ ጀምበር እቶን እሳቷን ከምታራግፍባቸው ነዲድ የሚተፉ በረሃዎች ውስጥ ከመሸጉ የነጻነት ፋኖዎች የምንጊዜም ጀግና የኢትዮጵያ ልጆች ጋር እንጂ፡፡ እነዚህ የነፃነት አርበኛ ውድ የኢትዮጵያ ወጣቶች ትምህርታቸውን፣ ስራቸውን፣ ስልጣናቸውን፣ ትዳራቸውን፣ አንዳንዶቹ ልጆቻቸውን… ባጠቃላይ የተደላደለ ኑሯቸውን ትተው ከአገርቤት፣ ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ በረሃ የወረዱት ለኢትዮጵያ ህዝብ ነፃነት ሲሉ ብቻ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት፣ ነፃነት፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ሲባል ክቡር ህይወታቸውን ዋጋ ለመክፈል ተዘጋጅተው በሃሩር እየነደዱ ቁራሽ ቂጣ አሸዋና ጭቃ በተቀላቀለበት ድፍርስ ውሃ አወራርደው ከዘንዶ፣ እባብና ጊንጥ ጋር እየታገሉ ውለው የሚያድሩ ናቸው፡፡ ዛሬ የዋጣቸውን ጥቅጥቅ ጨለማ ሳይሆን ከተራራው ወዲያ ከአድማስ ማዶ የምትታየውን፣ የነፃነት ጎህ የቀደደባትን፣ የነገዋን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ አሻግረው እዕምሯቸው ውስጥ በሚገኙ ትልልቅ ዓይኖቻቸው እየተመለከቱ መንፈሳቸው በፅናት የተሞላና ነብሳቸው በፍስሃ የተጥለቀለቀች ታሪክ ለመስራት የሚሻሙ ሀዋሪያዎች ናቸው፡፡ ከግማሽ ምዕተ ዓመታት በላይ ሲንከባለል የመጣ የህዝብ የነፃነት ጥያቄ ከትከሻቸው ላይ ያረፈ ለህዝብ ሲባል ልክ አንደ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ሞትን ገጥመው ያሸነፉ የዚህ ትውልድ አካል ናቸው፡፡ ስልጣን ፈላጊነት፣ ማናቸውም ቁሳዊ ፍላጎቶችና ልክ እንደ ደደቢቱ ህ.ወ.ሓ.ት ከህዝብ የተደበቀ ስውር ዓላማ ፈፅሞ የሌላቸው አልፋና ኦሜጋ የሆነ ታሪክ በደማቸው ለመፃፍ ከሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተፈጥረው በአንድ ዓላማ ዙሪያ በመሰባሰብ በአንድነት የቆሙ ንፁህና ጭቁን የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው፡፡ ይሄንን እውነት የኤርትራ በረሃ ተራሮች፣ በአፅም ስብርባሪ የዳበረው አፈር፣ ሳር ቅጠሉ ጭምር አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ ስልጣንና ቁሳዊ ፍላጎት ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ እንጂ በኤርትራ በረሃዎች ውስጥ አይደለም፡፡ ስልጣንና ገንዘብ ለማግኘት የሚያስፈልገው ህሊናን ሸጦ ከወያኔ መጠጋት እንጂ በረሃ ወርዶ አፈር ላይ መተኛት አይደለም፡፡ ይህ ከበረዶ የነጣ ሀቅ ደግሞ ነገ በተግባር ይገለፃል፡፡

ስለሆነም የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ከአንተ ተፈጥረው፣ ላንተ ነፃነት ብለው፣ አንተ የጉልበታቸውና ኃይላቸው ምንጭ ስለሆንክ በአንተ ተመክተው፣ ለአንተ ለመሞት ቆርጠው በረሃ የወረዱ ጀግኖች ልጆችህን ነው ህ.ወ.ሓ.ት ከጎኔ ተሰልፈህ ውጋቸው እያለህ የሚገኘው፡፡ ወያኔ የሚያደርገው ጦርነት አንተ ነፃ ሳትወጣ ወደፊትም በባርነት ቀንበር አንገትህን ታንቀህ በዘረኛ አገዛዝ ስር እድሜ ልክህን እየማቀቅህ እንድትኖር ሲባል የሚደረግ ነው፡፡ ይህ ነው እውነታው እወቀው…

ወያኔ በኤርትራ በረሃዎች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ብረት ያነሱ የነፃነት ኃይሎችን ከኤርትራ ጋር በሚደረግ ጦርነት ስም ለመደፍጠጥ የጦርነት ፕሮፖጋንዳ ወጀብ ማስነሳቱ ያለህዝብ ድጋፍ በወታደርና ጦር መሳሪያ ብዛት አንድ ስንዝር እንደማይራመድ ጠንቅቆ ስለሚያውቀው ነው፡፡ አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች፡፡

ምናልባት ሁሉም ህዝብ ጠለቅ ብሎ ላያውቅ ይችላል አላጥሽ፣ ማይካድራ፣ አዲ ጎሹ፣ በረከት፣ ሉግዲ፣…. ላይ በሚመሩት ሰራዊት ላይ የነፃነት አርበኞች የፈፀሙትን የህ.ወ.ሓ.ት ጀነራሎች እነ ሳሞራ የኑስና ሳዕረ መኮንን አሳምረው ያውቁታል፡፡ በእርግጥ የእነሱ ሰራዊት ይሁን እንጂ ታጭዶ አስከሬኑ መሬት ላይ የተነሰነሰው ጭቁን የድሃ ልጅ ነው፤ ያውም በዘር ወንፊት ተነፍቶ በእሱ ደም ምኒልክ ቤተ መንግስት ለመሰንበት እሳት ውስጥ የተማገደ፡፡

በሁለትና ሦስት ታጋይ እንደበግ የሚነዳ ሰራዊት፤ ገና የጥይት ድምፅ ሲሰማ ከተኛበት ተነስቶ በውስጥ ሱሪ ብቻ ከካምፕ ወጥቶ ወደ ከተማ እግሬን አውጭኝ የሚል፤ ከሆነ ቦታ ተነስተው ታጋዮች ወደ እሱ እየገሰገሱ እንደሆነ ሲሰማ ገና ሳይደርሱበት በርቀት ከባዶ ሜዳ ተኩስ ከፍቶ ጥይቱን በመጨረስ ተኩላ እንዳየ የበግ መንጋ በርግጎ የትሙን በመበታተን የሚጠፋ… መከላከያ ሠራዊት እንደሚመሩ የህወሓት ጀነራሎች በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ሰራዊቱ በጠቅላላ ከጓድ ጀምሮ እስከ ዕዝ ድረስ ተመሳሳይ ቋንቋ በሚናገሩ የህ.ወ.ሓ.ት ታማኝ ሰዎች ተጠርንፎ ሳይወድ በግድ በጉልበት የተያዘ እንጂ እሺ ብሎ በፍላጎቱ እንደማይዋጋላቸውም ጭምር የህ.ወ.ሓ.ት ጀነራሎች በጠቅላላ ያውቃሉ፡፡

አዎ በኢሳት ቴሌቪዥን በምሬትና በወኔ ሲናገሩ የሚታዩት የነፃነት ታጋዮች እንደ አኬልዳማና ጃሃዳዊ ሀረካት ለፕሮፖጋንዳ ሲባል ብቻ የሚተውኑ የቴአትር ገፀ-ባህሪያት አይደሉም በገሃዱ ዓለም በኤርትራ በረሃዎች ውስጥ በእውን የሚገኙ እንጂ፡፡ ምሬትና ቁጭታቸው እንዲሁም ወያኔን ለመደምሰስ ያላቸው ወኔ በቴሌቪዥን ስክሪን ከሚታየው በእጅጉ የላቀ ነው፡፡

ትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎችን እየመረጥክ በሰላም ወረዳ በማስቀረት ሌሎችን አንተ የእኔ ወገን አይደሉም የምትላቸውን ጭቁን የኢትዮጵያ ልጆች የሆኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ወደ ጦርነት የምትልከው “መንግስት” ወያኔ ሆይ! ለምን ኤርትራ ድረስ በመዝመት መንገድ ትመታለህ አርበኞች ግንቦት 7… አዲስ አበባ ድረስ ሊመጡልህ አይደለም ወይ…Deginetu Zewdu Abebaw

Elections: Damn if You Do, Damn if You Don’t!

Boycotting Ethiopian National

January 30, 2015

by Messay Kebede

I maintain that the upcoming elections will be a turning point for Ethiopia, not because they will result in a major change of policy subsequent to a renovation of the ruling elite but because the absence of change will compel opposition groups to reassess their strategies and the country as a whole will plunge further into the abyss of despair. While most reasonable people and opposition parties never contemplated the possibility of wining the elections and becoming the new ruling majority, nevertheless the expectation was—since the death of Meles Zenawi—for some opening, however narrow, to accommodate opposition groups. In light of the prevailing heightened repression and disqualification of some opposition parties from the competition by concocting bogus charges, the expectation proved utterly naïve. It is now patently clear that the EPRDF will use all available means to preserve the status quo indefinitely.

Opposition parties are already variously reacting to the perceived decision to exclude them once again. Some areBoycotting Ethiopian National Elections making their participation conditional on the change of policy of the National Election Board toward a neutral stand guaranteeing a level of playing field. Others have decided to participate regardless of the prevailing conditions because they believe that nothing can be achieved by shunning the elections. Still others seem undecided or are waiting for the development of the situation before taking a definitive stance. This article analyzes the cons and pros of participating in the upcoming elections with the view of showing the realistic alternative that emerges from taking part in the elections or boycotting them.

Let us state plainly the emerging quandary. Admittedly, the goal of participation is not to win, not because the regime is popular and has the allegiance of the majority of voters, but because it will use threat, harassment, deceit, and even violence to retain its present position, which is that only one parliament member is representing the opposition. The opposition may even lose this one seat or add some more, but the retention of an overwhelming majority will be the inevitable outcome of the elections. If so, why then participate when there is no the slightest opportunity to perform better?

Expected Gains from Participation

Those who opt for participation argue that winning has many forms. Indeed, elections, even if they are unwinnable, provide a good opportunity to denounce the regime. They supply a convenient platform to openly expose the failures and injustice of the regime at a time when popular attention and expectations are activated by the government’s own propaganda and its desire for renewed legitimacy. Exposing the regime is a vital component of nonviolent opposition. It is inconsistent to stay away from elections because the regime in place does not allow a fair playing field even as the purpose of peaceful struggle is, precisely, to mobilize voters to protest against the unfair conditions of political competition. Only such protests can bring about change, not boycott.

Parties that participate in elections find a good opportunity to promote themselves and make their program known to the public. Not only does participation help the recruitment of new members, but it also engages the party in the typical task of organizing and mobilizing the people. A party that is absent from the battle field on the pretext that conditions are highly unfavorable does not deserve to be called an opposition party, all the more so as it came into existence primarily to fight for the democratic opening of the political system.

To encourage people to oppose the regime, it is imperative to show the availability of an alternative program. If people are not exposed to the ideas of a viable organization and alternative policy, their legitimate fear of the unknown, including the possibility of a chaos, will prevail over their frustrations and make them stick to the status quo. Nothing extends more the life of unpopular governments than the lack of an alternative: such governments will always claim that the opposition is fearful to participate because it is too weak or has no viable rival program. And nothing shortens more their existence than the presence of a party that continues to fight against all odds. So that, in willingly participating in elections that are decided in advance, the opposition party demonstrates its full commitment, thereby changing its alleged weakness into the strength of steadfastness.

There is no telling in advance whether participation does not result in the gain of some seats. However limited, seats in the parliament offer the opportunity of voicing opposition from within the system, not so much to change the ongoing policy as to give more credibility to the availability of an alternative path. Parliamentary representation officializes opposition in the eyes of the people as well as of the government, forcing the latter to respond to criticisms instead of simply dismissing them as the views of outcasts.

To sum up, participation in elections, even when they are completely unfair, is not devoid of appreciable gains. In addition to being consistent with the choice of nonviolent opposition, it provides a much needed forum for opposition parties to convey their messages, mobilize voters, and strengthen their standing. By contrast, the rejection of elections until acceptable conditions emerges is defeatist and inconsistent with peaceful opposition, not to mention that it obtains and change nothing.

Expected Gains from Non-Participation

Naturally, those who favor boycotting the elections are not without some expectations of gains as well. To the extent that their decision is a political one, it must contain the possibility of advancing their cause in some way. So what do they expect to achieve in shining the elections?

Their main argument is that non-participation of opposition parties deprives the government of the legitimacy that it seeks by organizing these elections. Participating without the chance of winning even one seat is nothing but a free gift to the government. In advertising the pitiful result of the opposition, the government will have the easy game of declaring a crushing victory and portraying the opposition as irrelevant, nonexistent.

To take part under the existing conditions is to encourage the government to continue the same electoral policy. The only leverage that opposition parties have is that the government wants popular legitimacy by all means so that it is suicidal to give it up for what is nothing but a staged show to fool the Ethiopian people as well as the international community. Since opposition parties cannot expect anything unless existing conditions change, the kind of pressure liable to yield some results is precisely to make their participations conditional on some concessions on the part of the government. For this pressure to succeed, there is one and only one condition: the boycott must be unanimous and firm.

Experience teaches us that taking part in the elections under existing conditions will not result in any gain of parliamentary seat. Recall what happened to the All Ethiopian Unity Party in the 2010 elections: it broke away from the rest of the opposition by agreeing to participate without any tangible reforms of the electoral process only to find out that it was unable to secure even one seat despite its undeniable popularity in the Amhara region. What is more, opposition parties that already had some seats were completely wiped out. Obviously, the refusal of the government to make changes in the electoral process is motivated by a deliberate policy of expulsion of the opposition, and not by the precaution of having a sizeable majority.

As to exposing the anti-democratic nature of the regime, what else is more resoundingly revealing it than the refusal to participate in fake elections? By openly stating that participation depends on the creation of a level playing field, opposition parties do their primary job, namely, the presentation of reasonable and expected demands that normally go along with the very idea of holding elections. If elections do not have a minimum of fairness, they cease to be elections and turn into an exercise of canonization. The least that opposition parties can do is to put an end to this quinquennial farce.

Critical Assessment

What is striking about the above position is the belief that the refusal to participate puts pressure on the government. It would have been so if the opposition were united and the boycott unanimous. But to expect unity and a unanimous position is to assume solved the very problem that keeps the TPLF in power. Those who speaks of pressure put the cart before the horse by forgetting that the persistence of the hegemony of the TPLF is due to the success of its divide-and-rule policy, essentially manifested by the ethnicization of Ethiopia. Moreover, I do not remember a case where this government changed its opinion because of popular protests, let alone because of complaints from opposition parties. In other words, as hard as it may seem to accept, opposition parties have no leverage on this government.

True, the government wants legitimacy, but it can obtain it in various ways. For instance, it can force people to vote in great number so as to compensate the lack of opposition parties with a massive popular endorsement. Dictatorial regimes have practiced and refined this method for quite some time. If at all costs the presence of an opposition is required, the government can create fake opposition parties or divide existing parties by means of threats and bribes. This should not come as a surprise since the government has already given us the taste of such methods, just as it is presently doing it by prohibiting two major opposition parties, namely, Unity for Democracy and Justice Party and All Ethiopian Unity Party.

Given these available recourses, we can say that the government wants legitimacy, but not to the point of making concessions to the opposition. All the more reason for saying so is that legitimacy is essentially sought to shore up its international reputation, especially in the eyes of donor countries. Unfortunately, we have seen time and again that foreign countries, including democratic countries, are more interested in doing business than in denouncing and punishing undemocratic regimes.

To demand repeatedly for something and repeatedly obtain nothing, to the extent that it reveals the absence of leverage on the government, is easily construed as a demonstration of insurmountable weakness and inability to emerge as an alternative. What else can the people conclude from this constant failure to put pressure on the government but the utter weakness and irrelevance of the opposition? Since the opposition cannot extract the slightest concession from the government, there is no reason for the people to side with the opposition and become the target of government retaliation. Voting for the government may not bring change but at least it protects against retaliation.

As a matter of fact, neither participation nor boycott adds anything to the goal of denunciation for the simple reason that the anti-democratic nature of the regime has long ceased to be a mystery to foreigners or natives. If we still find Ethiopians who are not aware of its real nature, such people are better left alone since they are either irremediably apolitical or indifferent to what is going around them.

What about mobilization and organization? Does participation, as claimed by those opposing boycott, serve to strengthen opposition parties? It would have been so if the government would allow freedom of expression and organization. Such disposition would mean that the government is ready to face opposition in a level playing ground. But the very dilemma over participation stems from the knowledge that the government will not allow a condition of fair competition, that it will paralyzed the opposition by restrictions, harassments, and imprisonments, not to mention the silencing of the free press. To expect the strengthening of the opposition as a result of participation is just a wishful thinking.

The likely outcome being that participation will not bring any result, it removes the grounds for complaint about the lack of democracy. Your participation was a defiance intent on showing that you can pierce the barrier of exclusion. Your failure to do so only exposes your weakness and irrelevance. The aim of the government is not to show its strength by winning elections; rather, it is to display overtly that it has no real rivals worthy of that name. It does not want to win majority votes; it wants to ridicule the opposition by a crushing victory, thereby showing that there is no alternative to its rule. The proper analogy expressing Ethiopian elections is two soccer teams competing with the players of one of the teams being blindfolded.

In fact, a clear pattern emerges from the manner the government deals with opposition parties. Plainly, the government steps up its repressive power when it confronts unitary parties, such as the Unity for Democracy and Justice Party and All Ethiopian Unity Party, while being more tolerant of opposition parties with an ethnic banner. In ruthlessly repressing unitary parties, the government wants to bring about their final demise. The relative tolerance of the government to ethnicized opposition parties is, for sure, due to the perception of some affinity with its own policy; more importantly, however, it originates from the conviction that ethnic parties, fragmented as they are, can never become a threat to the hegemony of the TPLF. Add to this that it is simply easy to create hostility between these parties and reduce them to the permanent status of a negligible opposition.

The real threat, if fair elections were held, comes from unitary parties, as demonstrated by the success of Kinijit in 2005. In the eyes of the TPLF, Ethiopian nationalist parties cannot be allowed to grow, for the real enemy to its hegemony–which rests on the efficient implementation of divide-and-rule policy–is none other than Ethiopian nationalism. It is amazing that more than 20 years of uninterrupted attack and stifling have not succeeding in weakening Ethiopian nationalism. It has become the forbidden fruit: the more you want to muffle it, the more people want it.

Who Wins?

What springs from all is clear enough: opposition parties, whether they participate or not, lose in that none of the projected goals ascribed to participation or boycott is achievable. Neither participation nor boycott affects the standing of the government or the state of opposition parties in any meaningful way. Does this mean that the government win?

One thing is sure: after the elections, the government will not be better off. Not only will it face the same problems, but also its intransigence and repressive policy will heighten popular frustration and instill the sense of a political deadlock in the county. In other words, there is no winner, but only a huge loser, namely, nonviolent, peaceful opposition. Seeing the complete ineffectiveness of participation or boycott, people, especially the young, are increasingly bound to question the wisdom of peaceful opposition. The more repression continues, the more the deadlock over the possibility of change thickens, and the higher becomes the disposition toward uprising as the only alternative left. This is the iron law of all social blockage: Ethiopia will not be an exception.

When uprising becomes the only way out, young activists go underground or join armed struggle. Exciting nonviolent parties, too, to the extent that they are serious about the struggle for change, will be compelled to have a hard look at their strategy. Even if they continue to operate in a legal manner, it is no longer to win seats in the parliament. Instead, they anticipate uprising and hope to take its leadership when it erupts. Without doubt, the present attitude of the TPLF gives Ethiopians no other choice than revolution with, alas, the unpredictable but certainly severe and uncontrollable consequences that confrontation or civil war will have in present-day Ethiopia. Ethiopians, gear up for the worst!

ከኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ እና የኢትዮጵያ ኣርበኞች ኣንድነት ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

ጀግናው የኢትዮጵያ ህዝብ  ከወራሪ ሃይሎች ጋር ተፋልሞ ድል ያስመዘገበው ለነጻነቱ በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ምክንያት ነው።  የዚህ ታላቅ ህዝብ ተጋድሎ ለኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ለመላው ኣፍሪካ ህዝብ የነጻነት ፋና ወጊ ሆኗል።

ይህ ለነጻነት የተከፈለ ትግልና ዉጤቱ እንዲሁ በቀላል ነገር የመጣ ኣልነበረም። ሁሉም የኢትዮጵያዊያን ልጆች ዘር ሃይማኖት ብሄር ቀለም ሳይለዩ ባንዲት ባንዲራና ባንዲት እናት ኣገር ኢትዮጵያ ስም ተሰባስበው ኣንድ ልብ ኣንድ ኣላማ ይዘው ስለታገሉ እንጅ። በዚህ ምክንያትም የኣገራችን መላው ህዝብ በየትኛዉም ቦታ እራሳቸዉን ቀና ኣድርገው የሚሄዱ ነበሩ። በኣሁኑ ወቅት ግን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከመቸዉም ጊዜ በከፋ ሁኔታ የነጻነት እጦት ዉስጥ ተዘፍቆ ይገኛል። ያ ነጻነት የለመደ ህዝብ !ያ ተባብሮ በሰላም መኖር ልማዱና ባህሉ ያደረገ  ኩሩ ህዝብ! ዛሬ ግን በነጻነት እጦት ስር ወድቆ ከኣኩሪ ታሪኩ ጋር ወደታች እየሰጠመ ይገኛል። ወያኔ ኢህኣዴግ በዘራው መርዝ ምክንያት እርስ በርሱ ተለያይቶና ተፈራርቶ እንደጠላት እየተያየ ይገኛል።

ከሃያ ሶስት ኣመት በላይ  ሰላም  ኣጥቶ ነጻነት እንደተጠማ  ኑሮዉን እየገፋ ነው የሚታየው። በህወሃት ኣገዛዝ እየተንገፈገፈ ቢሆንም ተባብሮ ግን ከላዩ ላይ የተሸከመዉን የመከራ ሸክም ሊያራግፈው ያልቻለው በከፋፋይ ወያኔ መራሽ የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ ገመድ ተጠፍሮ  ስለተያዘ እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል። ለዚህ መፍትሄዉ ደግሞ የተባበረ ትግል  እንደሆነ በጽእኑ እናምናለን።

የነጻነት እጦት የወለዳቸውና  የኢትዮጵያን ህዝብ ከጭቆና ቅንበር ለማላቀቅ የሚታገሉ በርካታ ድርጅቶች እንዳሉ የሚታወቅ ነው። የትግላቸው ዉጤት ግን ግቡን ኣልመታም። ሁላችንም ታጋይ  ድርጅቶች ለምን ስንል ራሳችንን የምንጠይቅበት ወቅት ላይ እንዳለን የኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ ያምናል። የዚህ ጥያቄ መፍትሄ ኣቅጣጫ ደግሞ ወደ ኣንድነት የሚወስደን ይሆናል። ያለ ኣንድነት የቱንም ያህል ብንታገል የምንፈልገዉን ዉጤት ልናመጣ እንደማንችል ያሳለፍናቸው የትግል ጊዜያቶች ኣሳይተዉናል።

የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ንቅናቄ /EPUM/ ጋር በጋራና በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሷል። ታህሳስ 20 \2014 በጀርመን ኑረንበርግ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ህዝብ  ኣርበኞች  ግንባር ዘብ ኣምስተኛ ኣመት የምስረታ በኣል ላይ የሁለቱ ድርጅቶች ባንድ ኣመራር ጥላ ስር መጠቃለላቸው ይፋ ሆኗል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብ ሊቀ መንበር የሆኑት ኣቶ ልኡል ቀስቅስ የዉህደቱን ኣስፈላጊነት ኣስመልክተው የሚከተለዉን ብለዋል-

<<ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰላም ዴሞክራሲና ልማት ሰፍኖ ማየት የምንሻ ሁላችንም ኣገር ወዳድ የትግል ድርጅቶች እስካሁን ባካሄድናቸው የትግል እንቅስቃሴወች የምንፈልገዉን ዉጤት ማምጣት ኣልቻልንም። ለዚህም ዋናው ምክንያት ተባብረን ኣለመታገላችን ነው። ይህም ለወያኔ ምቹ ሁኔታን ፈጥሮለታል። ካሁን በሁዋላ ግን ኣካሄዳችንን ቆም ብለን ኣይተን በመተባበር ኣምባ ገነኑ ስርኣት እንዲወገድ ማድረግ መቻል ኣለብን። ከዚያ በተረፈ ምርጫ በመጣ ቁጥር የምናደርገው እንቅስቃሴና የተናጠል ትግል የትም እንደማያደርሰን ልንገነዘብ ይገባል። የኢትዮጵያ ህዝብ ኣርበኞች ግንባር ዘብና የኢትዮጵያ ኣንድነት ንቅናቄ ያደርጉት ዉህደት ፈር ቀዳጅ ነው >> ብለዋል።

በዉህደቱ ላይ የተገኙት  የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ንቅናቄ /EPUM/ ሊቀ መንበር የሆኑትአቶ ጥላሁን ገላው በበኩላቸው በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ እና የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ንቅናቄ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን  ይፋ አድርገዋል። ስለዚህ በኢትዮጵያ አንድነት ከሚያምኑ ጋራአብሮ የመስራት አላማ እንዳላቸው ያረጋገጡት የኢትዮጵያ አርበኞች አንድነት ንቅናቄ ሊቀ መንበር ሌሎች ድርጅቶች፣ ቡድኖች፣ ግለሰቦችና በብሄር ደረጃ የተደራጁ ድርጅቶች በጋራ ለመስራት ወቅቱ ስለሚያስገድድ በጥምረት ለመስራት  ከተስማሙት ድርጅቶች  ጋር ለመስራት እንዲመጡ ጥሪ አድርገዋል::

በመላው ኣለም የምትገኙ የድርጅታችን ኣባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያን የሁለቱን ድርጅቶች ዉህደት ተገንዝባችሁ ከጎናችን እንድትቆሙና ኣስፈላጊዉን ትብብር እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

ድል ለኢትዮጵያ ::

“ሕወሀት ኢሕአዴግ” በቅርብ ጊዜ የብሔራዊ እርቅ ተማጻኝ! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

September 4, 2014

ብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) በተለይ በእርስ በእርስ ግጭት ደም የተቃባንና የከፋ አደጋ የተጋረጠበትን ኅብረተሰብ ወይም የመበታተን አደጋ የተጋረጠባትን ሀገር በይቅር ለእግዚአብሔር ይቅር አባብሎ ሰላም ለማውረድና የቂም በቀልን ዶሴ ዘግቶ በአዲስ መንፈስ ብሔራዊ መግባባትን (National Consensus) ፈጥሮ የአንዲት ሀገርን ሕዝብ በአንድነት አስተባብሮ ለማንቀሳቀስና ህልውናውን ከመረጋጋቱ ጋራ ለማስቀጠል ዓይነተኛ መንገድ ነው፡፡

በሕወሀት ኢሕአዴግ የአገዛዝ ዘመን የዚህ የብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) ጥያቄ በተለያዩ አካላት በተደጋጋሚ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን የአገዛዝ ሥርዓቱ ይህ እርቅ ቢፈጸም የመጀመሪያውና ዋነኛው ተጠቃሚ እሱ መሆኑን እስከአሁንም ቢሆን መረዳት ባለመቻሉ ምክንያት የተለያዩ የእብሪት ኃይለ ቃሎችን በመሰንዘር ከተለያዩ ወገኖች ለሚቀርብለት ጥያቄ ቀና ምላሽ መስጠት ሳይችል ቀርቷል፡፡ የዚህም ምክንያቱ አንደኛ የሥርዓቱ ባለሥልጣናት የሌላው ጉድፍ እንጅ የራሳቸው ግንድ ስላልታያቸው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ቀኑ ለእነሱ “ሁልጊዜም ፋሲካ” እንደሆነላቸው የሚኖርና አይቀሬው ነገር ማለትም ቀን ተለውጦ ትላንት በሌላው እጅ የነበረው ዛሬ በእነሱ እጅ ያለው ነገ ደግሞ በሌላው እጅ እንደሚገባ ያለመረዳትና ዘለዓለም በእነሱ እጅ የሚኖር ስለመሰላቸው የፈጠረባቸው መዘናጋት ናቸው፡፡

በእኔ እምነት ይህ ትንሽዬ አገዛዝ የቀረበለትን ወርቃማ እድል ሊጠቀምበት ሳይችል ቀርቶ በማባከኑ ከጉዳዩ ተጠቃሚ ሊሆን የሚችልበትን እድል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳመለጠው አስባለሁ፡፡ አርቀው ማሰብ ቢችሉ ወይም የያዙትን የኃላፊነት ቦታ የሚመጥን ጭንቅላት ቢኖራቸውና ነገ ሌላ ቀን ነው ብለው ጥያቄውን በቀናነት ተቀብለው አስተናግደውት ቢሆን ኖሮ ለሁሉም መልካም ተአማኒ ሰላም ለሀገርም የጸና መሠረት ያለውና ትክክለኛ የዲሞክራሲ (የበይነ-ሕዝብ) ሥርዓት ለመመሥረት በተቻለ ነበር፡፡
ይህ እድል በወያኔም ባይሆን በሌላ ለሀገሪቱና ለሕዝቧ እንደሚኖር አትጠራጠሩ፡፡ ለወያኔ ግን ኃጢአቱን ሊያሥተሰርይለትና በኢትዮጵያ ታሪክ መልካም ስም ሊያሰጠው የሚችለውን መልካም ታሪክ ሠርቶ ማለፍ የሚችልበት ቀን አለፈ፡፡ እስከዛሬ ይህ ትንሽዬ አገዛዝ ተለማኝ ሌሎች ወገኖች ማለትም የሲቢክ (ሕዝባዊ) ማኅበራትና ፖለቲካዊ (እምነተ-አሥተዳደራዊ) ማኅበራት ደግሞ ለማኝ ነበሩ፡፡ እመኑኝ አትጠራጠሩ ከዚህ በኋላ ግን ለማኙ ወያኔ ተለማኙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሆናል፡፡ አዲሱን ዓመት 2007ዓ.ምን ጨምሮ ቀጣዩ ዓመት ለወያኔ ጭንቅና ጥብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደግሞ ተስፋን ይዘው መጥተዋል፡፡

ከዚህም የተነሣ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወያኔ ይሄንን ብሔራዊ እርቅ እሱ በሚመቸው መንገድ አጠናቆ ከጉድ ከውርደትና ሞት ለመዳን የሚችልበትን ስልት በመንደፍና ጭንቅ በገጠመው ቁጥር እየሰበሰበ የሚያሠማራቸውን ከጭንቁ የሚታደጉትን “የሀገር ሽማግሌ” ተብየዎችን ቀሳጢ ጉዳይ አስፈጻሚዎች በማሠማራት ውትወታውን እንደሚያጧጡፈው “ምናለ አምሳሉ በሉኝ” ጠብቁ፡፡ በእኔ እምነት ሕወሀት ኢሕአዴግ ይሄንን ታላቅ ብሔራዊ ቁምነገር መከወን የሚችልበት አቅም ትከሻ ቅድስናና ሰብእና ቅንጣቱ እንኳን የለውም፡፡ በሕወሀት ኢሕአዴግ ከዋኝነት አስተናጋጅነት ኃላፊነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሊመጣ ሊገኝ የሚችል መሠረት ያለው እውነተኛና ትክክለኛ ሰላምና እርቅ አይኖርም፡፡ ምክንያቱም አንዴ ሁለቴ ሦስቴ ብቻም አይደል ለቁጥር ለሚያዳግት ጊዜ መንግሥት ነኝ ከሚል አካል ፈጽሞ በማይጠበቅ ነውረኛነት ብልግና እብለትና ክህደት ማጭበርበር ማወናበድም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተደጋጋሚ ጊዜያት ስለተካደና ስለተሞኘ ስለተወናበደና ስለተጭበረበረ ወያኔ መታመንን መልሶ ላያገኘው አጥቶታልና ብቻ ሳይሆን ወያኔ ይሄንን ማድረግ የሚችልበት ተፈጥሮ ወይም ሰብእና እንደሌለው ሕዝቡ በሚገባ ያውቃልና ነው፡፡

አሁንም እርግጠኛ ነኝ ወያኔ ይሄንን አስመሳይ እንቅስቃሴ በሚጀምርበት ጊዜ በተቃውሞና በፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ያሉ የሥልጣን ጥማት ያስቸገራቸው ዜጎች በአገዛዙ በመደለል የእንቅስቃሴው አባሪ ተባባሪ ሆነው በመራኮት በሀገርና በሕዝብ ዘላቂ ጥቅም ላይ ከባድ ስሕተትና በደል የሚፈጽሙ ግለሰቦችና ቡድኖች እንደሚኖሩ አትጠራጠሩ፡፡ ምን አለፋቹህ የምታዩት ታላቅ ድራማ ይኖራል፡፡ ከዚህ በኋላ ከምሁራንም በሉ ከፖለቲከኞች እንዲሁም ከሀገር ሽማግሌዎች ባጠቃላይ ከሀገሪቱ ልኂቃን የብሔራዊ እርቅን ጥያቄ ለወያኔ አቀረቡ የሚባሉ ዜጎች ቢኖሩ ያለውንና የነበረውን የተፈጠረውንና የሚፈጠረውን ሁሉ ጨርሰው የማያውቁ ያልተረዱና የማይረዱ የዋሀን እንደሆኑ ልነግራቸው እወዳለሁ፡፡
ይሄንን ሐሳብ ያለ ምንም ግላዊና ከሀገር ጥቅም ጋር ከማይቃረን ምክንያት ከቀናነት ብቻ የሚያስቡ ዜጎች ካሉ እንደምኞታቸው ቢሆን ምንኛ መልካም በሆነ ነበር፡፡ ያለው ሀቅ ግን ከሚያስቡት እጅግ የራቀና የተለየ ነው፡፡ የሥርዓቱ ባለሥልጣናት በብዙ ቢሊዮን (ብልፍ) የሚቆጠረውን ከሀገሪቱ የመዘበሩትን ገንዘብ ቢመልሱም እንኳ፣ ለሀገር ለወገን በተቆጩ የዜግነት ግዴታቸውን ለመወጣት በታተሩ እየታፈኑ ተወስደውባቸው ልጆቻቸው ወላጆቻቸው በግፍ ተገለውባቸው ለመቅበር እንዲችሉ አይደለም ሞታቸውን እንኳን እንዳያውቁ ተደርገው እርማቸውን እንዲበሉ የተደረጉ ወገኖችን “ግድ የላቹህም ከሁሉም ነገር ሀገር ትበልጣለችና ስለ ሀገር ብላቹህ ይቅር በሉ” ብለን ማሰመን ብንችልም እንኳ፣ “በገደሉኝ በተሻለኝ” የሚያሰኙ ግፍና በደል የተፈጸመባቸውን ወገኖችንም እንደዚያው ማሳመን ብንችልም እንኳ፤ ሀገር ይቅር የማትለው ለይቅርታ የማይመች በርካታ የሀገር ክህደት ወንጀሎች አሉና ይህ የብሔራዊ እርቅ ሐሳብ ከወያኔ ጋራ ምንም የሚሆን አይደለም፡፡ በወያኔ የተደለሉ የተወሰኑ ወገኖች ተወናብደውና አወናብደው እንዲሆን ቢያደርጉ ግን ሀገሪቱ በኢፍትሐዊ መንገድ በወያኔ ያጣቻቸውን ብሔራዊ ጥቅሞቿን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቀን በወጣለት ጊዜ ሥልጣንን በእጁ ባደረገ ጊዜ እንዲመለሱለት ጥያቄ የማቅረብና ማስመለስ የሚችልበትን መብት እንዲያጣ ያደርገዋልና ከወያኔ ጋራ በዚህ መልኩ መሸኛኘት የማይታሰብ ነው፡፡

በየዋህነት እንደሚያስቡት ወገኖች በወያኔ እጅ ይሄ ቢፈጸም በኋላ ላይ ለማይወጣላቸው ጸጸት እንደሚዳረጉ ነገሩ እርግጥ ነውና ከወዲሁ መጠቀሚያ ከመሆን እንዲቆጠቡ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ለነገሩ የፈለገውን ያህል ቢባል በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በወያኔ ተሹመው እያገለገሉ እንደምናያቸው የትምህርታቸውንና የእድሜያቸውን ያህል የማያስቡ እንደ እንስሳ ያለ ሆዳቸው ምንም ነገር የማይታያቸው፤ ካለባቸው የአድር ባይነት ርካሽና ወራዳ ሰብእናቸው የተነሣ የዐፄ ኃይለሥላሴን የደርግን አሁንም ደግሞ የወያኔን ሥርዓት ወይም ደግሞ ደርግን ሲያገለግሉ ቆይተው አሁን ደግሞ የወያኔ ሹመኛ ሆነው ያለ አንዳች የአቋም ችግር እንደሚያገለግሉት ሆዳቸው አምላካቸው ክብራቸው በነውራቸው የሆኑ ግልሰቦችን እንደባዶ ብርጭቆ የሞሉባቸውን ሁሉ የሚሞሉ፣ በዚህ ርካሽና ወራዳ ማንነታቸውም ከሰው ፊት ሲቀርቡ ቅንጣትም እንኳን ሐፍረትና መሸማቀቅ የማይታይባቸውን ግለሰቦች አግኝቶ መንቀሳቀሱ አይቀርም፡፡ ምን ቢሠራ ምን ቢያደርግ ግን የሕዝብ አመኔታን አያገኝም እንጅ፡፡

ነገር ግን አገዛዙ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንቅሮ እንደተፋው አውቆ ምንም ቢያደርግ ተአማኒነት አግኝቶ ተጠቃሚ በሚሆንበት መንገድ የሚያደርገውን አስመሳይ ብሔራዊ እርቅ (National Reconciliation) መከወን እንደማይችል ከተረዳ ግን ጡንቻው ሊያቆየው እስከቻለለት ጊዜ ድረስ እየተንገታገተ ይቆይና የፍጻሜው ሰዓቱ ሲደርስ በየመቀመጫችን የቀበረብንን የዘርና የሃይማኖት የሰዓት ፈንጅዎች (Time Bombs) በማፈንዳትና ሀገሪቱን በማፈራረስ ለፍርድ የሚያቀርብ ጠያቂና ከሳሽ አካል እንዳይኖርበት ለማድረግ እንደሚሞክር ካላቸውና ከምናውቀው “ከእኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” ተፈጥሯቸውና ከእስከዛሬው ፀረ ኢትዮጵያ ሸራቸው በመነሣት መረዳት ይቻላል፡፡ ወያኔ ሁለቴና ሦስቴ አይደለም ሽህ ጊዜ እንኳን በምርጫ ቢሸነፍም ተሸንፌያለሁ ብሎ ሥልጣን የማያስረክብበትም ዋነኛው ምክንያት ይሄ ነው፡፡ ሥልጣን በለቀቀ ማግሥት በፈጸመው ግፍ፣ ሙስና፣ ወንጀልና የሀገር ክህደት ሁሉ እየታነቀ ለፍርድ እንደሚቀርም አሳምሮ ስለሚያውቅ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ወያኔ ከደገሰበት የጥፋት ድግስ አንጻር ሊጠነቀቃቸው የሚገቡ በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ይህ የወያኔ ሀገሪቱን አፈራርሶ የመጥፋት ሰይጣናዊ ተግባር እውን ይሆናል ብሎ ግን ቅንጣት ታክል እንኳን እንዳይጠራጠርና ሥጋት እንዳያድርበት ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ይህች ሀገር መቸም ጊዜ ቢሆን ባላት የሠራዊት ብዛትና ኃይል ብቻ በመመካት ከጥፋት የዳነችበት ወይም የተረፈችበት ዘመን ኖሮ አያውቅም፡፡ ይልቁንም በየበረሀው በየገዳሙ በየዋሻው በየፍርኩታው በየበዓታቸው ጤዛ ልሰው ቅጠል ቀምሰው ዳዋ ጥሰው ድንጋይ ተንተርሰው ግርምዓ ሌሊቱን ፀብአ አጋንንቱን ታግሰው በአስጨናቂ ጾም ጸሎት ሥግደትና የተለያዩ የመከራ ትሩፋት ስለ ተወዳጅ ሀገራቸውና ሕዝባቸው መከራ በመቀበል በሚያለቅሱት በቅዱሳኖቿ ጸሎትና ምልጃ እንጅ፡፡ ይሄንን ያህልም የተፈተነውና መከራ እያየን ያለነውም የእነሱን ጸሎት ፈጣሪ ስላልሰማ ወይም ስለማይሰማ አይደለም፡፡

የዚህ ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ላይ በዕብ. 12፤5-11 ላይ ይገኛል “ልጀ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቃልል በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል፡፡ ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታቹሀል፡፡ ለመቀጣት ታገሡ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርጋቹሀልና፡፡ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኗልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃሎች እንጅ ልጆች አይደላቹህም፡፡ ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋ አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይዎት ልንኖር በተገባን? እነሱ መልካም ሆኖ እንደታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል፡፡ ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጅ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል” ይላል ቃሉ፡፡ “የእስራኤል ልጆች ሆይ! እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላቹህምን? ይላል እግዚአብሔር” ትን. አሞ. 9፤7 በመሆኑም እኛ ኢትዮጵያዊያን ልጆች እንጅ ዲቃሎች አይደለንምና ምንም ቢበድሉ የቱንም ያህል ቢረክሱ ቢያምፁበትም ምንም እንደማይላቸው እንደ ሌሎች ሀገራትና ሕዝቦች ዝም አይለንም እሽ እስክንልና እስክንመለስ ድረስ ይቀጣናል፡፡

ትናንትና በቅዱሳኖቿ ጸሎትና ልመና እንደሚመጣባትና እንደሚደርስባት የፈተናና የመከራ ክብደትና ብዛት ሳያደርግባት እንደአመጣጡ እየመለሰ ከብዙ መከራና ጥፋት የታደጋት አምላክ ዛሬም አለ፡፡ በእርግጥ ቃሉ “እሽ ብትሉ ለኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላቹህ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላቹሀል” ትን.ኢሳ. 1፤19-20 እንዳለው ይህ ሁሉ ጉድ የመጣብንና የተሰበርነው እንቢ በማለታችን መሆኑን ሁሉም እያንዳንዱ ወደሌላው ሳይሆን ወደ ራሱ ወደ ውስጡ በመመልከት ምን ያህል እንዳመፅን እንደረከስን እንደበደልን ከውስጡ ከሚያገኘው መልስ የሚረዳው ነገር ቢሆንም ምን ብንበድለው ምን ብናሳዝነው እንዲህ ወያኔ ላሰበብን ለደገሰብን ዓይነት ጥፋት አሳልፎ ይሰጠናል ብላቹህ ቅንጣት ታክል እንኳን እንዳትሠጉ፡፡ “እመኑ እንጂ አትፍሩ”

ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በእግዚአብሔር ቸርነትና በራሱ በልጆቹ ጥረት ቀድሞ በመንቃት ከጫፍ እስከ ጫፍ ወያኔ የተከለብንን የዘርና የሃይማኖት ፈንጅዎቹን በማምከን ሌሎች እሾሆቻችንም በመንቀል በአዲስ መንፈስ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆኖ በመነሣት ከጥፋት ይድናል የሚል የጸና እምነት አለኝ፡፡ ለወያኔ የምንሰጠው ወይም የማንነፍገው ነገር ቢኖር ፍትሕና ሕትህ ብቻ ነው፡፡ ሁሉም የዘራውን ማጨዱ ግድ ነው፡፡ ቃሉም እንደሚል “ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና” ገላ 6፤7 ፡፡ እናም በብዙ ነገር የቆሰለውን የደማውን ያመረቀዘውን የሀገር አንጀት የሚያጠግገው ቂም በቀልን የሚሽረው ፍትሕ ብቻ ነው፡፡ ለዚህች ከቅርብ እርቀት ላለች ትንሣኤያችንን ለምታረጋግጠው ብሩህ ቀናችንም ታጋዩ አርበኛው ወታደሩም በጽናት ይታገል፣ ሁሉም ዓይነት ሠራተኛ በትጋት ይሥራ፣ ገበሬውም በብርታት ይረስ፣ ካህኑም በንጽሕና ይጸልይ ይቀድስ፣ እናቶችም ያለ እረፍት ይማለሉ፣ ሁሉም ዜጋ እጁ ላይ ባለው ነገር ሁሉ የመጨረሻ ይበርታ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

የትግል ጥሪ በውጭ ለመትኖሩ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ

የኢትዮጵያ ሕዝብ በወያኔ የአፈና ቀንበር ስር ከወደቀ አንስቶ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በማህበራዊ ሕይወቱ እጅግ ወደከፋ አቅጣጫ እያመራ ይገኛል በተለይም የመንደር ፖለቲካው በኢትዮጵያዊያን መካከል ለመፍጠር እየተሞከረ ያለው ልዩነት ስርዓቱ እንዳሰበውና እንደሚፈልገው ገቢር አይሁን እንጂ አገዛዙ የለኮሰውን የጥፋት እሳት በአፋጣኝ ተረባርበን ካላጠፋነው ለወደፊት በኢትዮጵያዊነት ስሜት እና መንፈስ ላይ አደጋ የሚፈጥር ነው።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር አምባገነኑንና ጎጠኛዉን የወያኔ አገዛዝ ለማስወገድ ከፍተኛ መስዋአትነት ከፍሏል። ድርጅታችን ለኢትዮጵያና ሕዝቧ ጥቅም ሲል ዳገት ቁልቁለቱን፣ ረሃብና ጥሙን፣ ውርጭ ቸነፈሩን የኔ ብሎ በመቀበል አጥንቱን በመከስከስ ደሙን በማፍሰስና መተኪያ የሌላት ውድ ህይወቱን በመክፈል ለአገሩና ለሕዝቡ ያለዉን ጥልቅ ፍቅር በተግባር አስመስክሯል ።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለለውጥ ትግሉ በሰላማዊ ሰልፍ ፣ በሻማ ማብራት፣ የወያኔን ድብቅ አጀንዳ የተለያዩ መንግስታት እንዲያውቁት በማድረግ፣ በማማከር፣በገንዘብ ወ.ዘ.ተ ድጋፍ በማድረግ ቀላል የማይባል ሚና ተወጥተዋል ።
ይህ የተቀደሰ የአርበኝነት ትግል በተደራጀ እና ወጥነት ባለው መልኩ እንዲከናወን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአቶ የዋርካው መንግስቱ የሚመራ የዓለም አቀፍ ኮሚቴ በጊዜያዊነት መቋቋሙን እያስታወቅን ኮሚቴው ግንኙነቱና አጠቃላይ የውጭ እንቅስቃሴዎቹ ከግንባሩ የውጭ ጉዳይ ሃላፊ አርበኛ ኑርጀባ አሰፋ እውቅናና ምክክር ይሆናል ከዚህ አሰራር ውጭ የሚደረግ ማንኛውንም አይነት የውጭ እንቅስቃሴ ግን ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን።
በተቋቋመው የዓለም አቀፍ ኮሚቴ ስር በመደራጀት መላው ዲያስፖራ የየበኩሉን ድርሻ በመወጣት ለስደት የዳረገውን የወያኔ አገዛዝ ለመታገል ነገ ሳይሆን ዛሬ ሊነሳ ይገባል።
አንድነት ሃይል ነው !
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር
ሐምሌ 14-2006 ዓ/ም