ጥብቅ መልእክትና ማሳሰቢያ ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ( አርበኞች ግንቦት ሰባትና ደህሚት ሰራዊት)

የአርበኞች ግንቦት ሰባትና ደህሚት ሰራዊት ዉድ የሆነችዉን ህይወታቸዉን ከፍላዉ ኢትዮጵያን ከዘረኛዉ፤ከከፋፋዪ፤ እዉነትና እዉቀት ከራቃቸዉ ጥቂት የባነዳ ልጆች ነፃ ለማዉጣትና የተከበረች፤ የተፈራች፤ ለዜጎቿ ምቹ የሆነች፤ ሁሎም ልጆቿ የሚቧርቁባትንና የሚበለፅጉባትን ኢትዮጵያን ለመመስረት ትግሉን መጀመሩን የሰማችሁ ይመስለናል፡፡ አገር ቤት ላለዉ ዘመዶቻችን መልእክቱን ንገሩ፡፡
በአርነኞች ግንቦት 7 አባል የማስተላልፈዉ ማሳሰቢያና ማስጠንቀቂያ የሚከተለዉን ይመስላል፡፡

1. በ ሚያዚያ ወር 2007 ዓም ወያኔ የግል የጦር መሳሪያ ምዝገባ እንዳካሄደ ይታወቃል፡፡ ይህን መሰረት አድርጎ በወያኔ ሎሌወችና ባንዳዎች መሰረት መሳሪያህን ሊያስወርድህ እንደሆነ ሰሞኑን ከአገኘሁት የደህንነት ሚስጥር አካፍልሀለሁ፡፡ ባነዳወችን በጥንቃቄ ተከታተል፡፡ ኢትዮጵያዊ ዋናዉ ጀግንነቱ ርስቱና ነፃነቱ የሆነችዉን የጦር መሳሪያዉን ለማንም ባንዳ የሚያስረክብ ስነ-ልቦና እንደሌላዉ ታሪካችን ያስረዳልና የታሪክ ተወቃሽ እንዳትሆኑ ንቁና ባንዳዎችን ተከታተሉ፡፡ ማንንም የወያኔ ባንዳ እንዳታምኑ፡፡ መሳሪያህን ሊያስወርድ ከሞከረ በቡድን ሁነህ ለነፃነትህ ሸፍት ፡፡ የወያኔ ሰራዊትን በቡድን ሁነህ በማጥቃት መሳሪያዉን ተረከብ ነገር ግን የወንድምህን ህይወት በከንቱ እንዳትቀጥፍ ተጠንቀቅ፡፡ ቤት ያፈራዉን መግበዉ ልብስም አልብሰዉ፡፡ የነፃነት ታጋዮችን እንዲቀላቀልም መንገድ ምራዉ፡፡

2. የወያኔ ቁጥር አንድ ተላላኪ ባንዳ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጦርነቱን ከወንድማችንና ከእህታችን የኤርትራ መንግስትና ህዝብ ነዉ ሲል 100 ፐርሰንት የግሉ ባደረገዉ የዝንጀሮዉ ምክርቤት ጋር መምከሩን በ ኢትዮጵያ ስም በሚነግድበት ቴሌቪዝንና ሬድዮ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ይህ የተለመደ ቀልድ ነዉ፡፡ ይህ የነፃነት ጦርነት 100 ፐርሰንት የምርጫ ካርዱን ከ 1997 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ምርጫ በተዘረፈዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆችና ጥቂት በስርአቱ የበለፀጉና የህዝብን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸዉ ካደረጉ ወያኔዎች፤ባንዳዎችና ተላላኪዎች መካከል እንጂ ከ ኤርትራ ህዝብና መንግስት ጋር አይደለም፡፡ የኤርትራን ህዝብ ሞክሩት እኛም ከጎናቸዉ እንሆናለን፡፡ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የቀለዳችሁብንን አንረሳዉም፡፡ የባድመ መሬት ሲወረር ሉአላዊ ግዘተችን ተወረረ ብላችሁ የጎንደር ድንበርን መሬት ለሱዳን ሰጥታችሁ ቁራጭ መሬት እያላችሁ መቀለዳችሁን አትርሱት፡፡ ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት ብትጨነቁ ሱዳን ላይ እንዝመት ትሉን ነበር፡፡

3. በአንዳን ከተሞች የትግራይን ህዝብ ይሁንታ ለማግኘት በግንቦት ሰባትና በሌላዉ ብሄር ስም ( በተለይም በአማራዉ) ወያኔ በትግረኛ ተናጋሪዎች ድርጅትና ነብስ በድብቅ በመግደልና ድርጅታቸዉን በቦንብ በማፈራረስ የትግራይ ህዝብ እንዲነሳና ሌላዉም ህዝብ ይህን እኩይ ተግባር በመኮነን ከነፃነት ታጋዮች እንዳይሰለፍ የተለመደ በሀዉዜን ህዝብ ላይ የሰራዉን ሴራ ሊሰራ መዘጋጀቱንና የዶኪመንተሪ ፊልምም ሊሰሩ ስለተዘጋጁ የትግይ ተወላጅ የሆናችሁና በሌላዉ ክልልና በትግራይ የምትኖሩ ትግረኛ ተናጋሪወች ጥንቃቄ እንድታደርጉ አደራ እንላለን፡፡ ወያኔ መቸዉንም ቢሆን መጀመሪያ የሚነግደዉ በእናንተ ደምና ስም ነዉ፡፡ ሌላዉም ብሄር በወያኔ ፕሮፖጋንዳ የደነዘዛችሁ በወንድሞቻችሁንና በእህቶቻችሁን ላይ ምንም አይነት እርምጃ እንዳትወስዱ አደራ እያልን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ከማኝኛዉም ጥቃት እንድትጠብቁና ኢትዮጵያዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን፡፡

4. ወያኔ ሰሞኑን ዉድ የኢትዮጵያ ልጆችን ለዚህ ቅዱስ ጦርነት በየቀበሌዉ ማስታወቂያ ለጥፎ እየመለመለ ወደ ስልጠና ጣቢያዎች ከማስገባቱም በላይ አምስት ወር ያለሞላቸዉን ሰልጣኞችን ወደ ግንባር እያመላለሰ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ልጆችህን ለዚህ የሰይጣን አማልክት ለሚከተሉ የባንዳ ልጆች እንዳትልክ ማስገንዘብ እንፈልጋልን፡፡ ግንባር ላይ ላለዉ ልጅህም መሳሪያዉን ወደ ባንዳዎች እንዲያዞር መልክት ላክ፡፡

5. ተደራጅታችሁ በሲቪል መስሪያ ቤቶችና በግል ተቋማት ዘረፋ ሊካሄድ ስለሚችል ባንኮችን፤ ሆቴሎችን፤ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ከዘረፋ ጠብቁ፡፡ ለተወሰነም ጊዜ ቢሆን ቤታችሁ ዉስጥ ችግር እንዳይኖር የምትመገቡትን አዘጋጁ፡፡ የደርግ መንድስት ሲወድቅ የትምህርት ቤት ወንበርና ጠረጴዛ የሀክምና ተቋማት ቁሳቁስ ሳይቀር መዘረፉን እንዳትረሳ፡፡ አገራችንን ከዜሮ መጀመር ሸክሙ ለእኛዉ ነዉ፡፡

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

Leave a comment